የቱሪዝም ዘርፍ የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገለፀ
(ነሐሴ 8/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የስልጢ_ቡታጅራ ጂኦ ፓርክ ክልላዊ ማስጀመሪያ መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ እንደተናገሩት እንደ ክልል በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ከዘርፉ ማግኘት ያለበትን ጥቅም ማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
በክልሉ 11 የቱሪስት መስህቦችን ለማልማት ፕሮጀከት ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን በመግለጽ መስህቦች ለምቶ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የገቢ ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።
ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የጂኦ ፓርክ የምክክር መድረክ ለቀጣይ ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ የሚረዳ እንደሆነም ተናግረዋል።
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ በበኩላቸው የቱሪዝም ዘርፍን ማሳደግ ለኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ የአካባቢውን ገፅታ ለመገንባትም የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
ከመድረኩ የስልጢ_ቡታጅራ ጂኦ ፓርክ ዙሪያ ለሚሰራው ተግባር የጋራ ግንዛቤ ይይዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩም ከቱሪዝም ሚኒስቴር የመጡ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
