Skip to main content

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2017 በጀት አመት የባለሙያዎችና የአቃቤ ህጎች የማትጊያና የእውቅና መርሃ ግብር አከናወነ!

የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የሴክተሩን የ2017 አመታዊ አፈጻጸም መነሻ ያደረገ የባለሙያዎችና የማትጊያና የአቃቤ ህጎች የእውቅና መርሃ ግብር አከናውኗል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ አቶ ሬድዋን ኑሪ በ2017 መምሪያው በፈጸማቸው ተግባራትና ባስመዘገባቸው ውጤቶች ላይ የተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች አሻራቸውን ማኖራቸውን አስታውቀዋል።

የተሻለ ለፈጸሙ ባለሙያዎች እውቅና መስጠትና ማበረታታት የተቋምንና የግለሰቦችን የመፈጸም አቅም እንደሚያሳደግ ያስታወሱት አቶ ሬድዋን ከዚሁ መነሻ የሴክተሩ የእውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር መሰናዳቱን ገልጸዋል።

በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞችና አቃቤ ህጎች በተለያዩ ዘርፎች ተከፍለው የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በዚሁ መሰረትም በአጠቃላይ ሰራተኞች፣ በሴቶች፣ በአቃቤ ህጎች እና ልዩ ተሸላሚ  በሚሉ ምድቦች የተቋሙ ሰራተኞች የማትጊያና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Image
የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ የ2017 በጀት አመት የባለሙያዎችና የአቃቤ ህጎች የማትጊያና የእውቅና መርሃ ግብር አከናወነ!