የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋና ፈጣን የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እንዲከበር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ፦ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ
(ነሐሴ 29/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፍትህ ትራንስፎርሜሽንና የፍርድ ቤቶች ጥምረት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የፍትህ ተቋማት ቀልጣፋ፣ፈጣን እና ዘመናዊ የፍትህ ስርዓትን በመዘርጋት ለዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶች እና ነፃነት እንዲከበር በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በፍትህ የተገልጋዩን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ ችግር ፈቺ ቅንጅታዊ አሰራሮችን የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል ያሉት ዋና አፈ ጉበኤዋ አገልግሎትን በተለመደ አሰራር ሳይሆን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለህዝብ ተጠቃሚነት መስረት ይጠበቃል ብለዋል።
የፍትህ ተቋም ተገልጋይ የሚበዛበት ተቋም በመሆኑ በፍትህ ተቋማት የሚስተዋሉ የስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ የግለጸኝነትና ተጠያቂነት ስርዓትን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
በቀጣይ ጥምረቱ ተግባራትን በዕቅድ በመምራት የግንኙነት አግባብን በማጠናከር በፍትህ አገልግሎት የረካ ህብረተሰብን ለመፍጠር መትጋት እንደሚጠበቅም ተናግረዋል።
የጥምረቱ ሰብሳቢ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ በበኩላቸው የሚንፀባረቁ ችግሮችን በመለየት ለህዝብ የፍትህ ተደራሽነትን ለማድረስ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል።
በቀጣይ አሰራሩንና ህጉን በመጠበቅ ጤናማ የሆነ የፍትህ ስርዓትን በመከተል ህዝቡ የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት መትጋት ይገባል ብለዋል።
የምክክሩ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት የፍትህ ስራ በአንድ ተቋም ብቻ የሚሰራ ባለመሆኑ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በተጠያቂነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ከህዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ አስፈጻሚ እና ፈጻሚ አካላት በተቀመጠው አሰራር መሰረት ህብረተሰቡ ትክክለኛ እና ቀልጠፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በባለቤትነት መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።
በአስፈጻሚ እና ፈጻሚ አካላት የሚስተዋሉ የስነ ምግብር እና የክህሎት ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ ኃላፊነትን በአግባቡ መወጣት ይገባል ነው ያሉት።
የክልሉ መ/ኮ
