የይቅርታ ቦርድ ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- በይቅርታ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት የሚቀርቡ የይቅርታ ጥያቄ ማመልከቻዎችን ይቀበላል፤ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ለይቅርታ ቦርዱ ለውሳኔ ያቀርባል፤
- የቦርዱን መዛግብትና ሠነዶች በአግባቡ ይይዛል፤ ይጠብቃል፤
- በቦርዱ የውሳኔ ሃሳብ የተሰጠባቸውን ሁሉንም ጉዳዮችና በርዕሰ መስተዳደሩ የፀደቁትን ውሳኔዎች በአግባቡ ይይዛል፤ ይጠብቃል፤ ስታስቲክስ ያዘጋጃል፤
- የይቅርታ ጥያቄዎችን በሚመለከት በቦርዱም ሆነ በርዕሰ መስተዳደሩ የሚሰጡ ውሳኔዎችን ይቅርታ ጠያቂው ለሚገኝበት ማረሚያ ተቋም ያሳውቃል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤ የይቅርታ ምስክር ወረቀት ይሰጣል፤
- ፍትህ ቢሮ እና ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በመሆን የሚያቀርቧቸውን የይቅርታ ጥያቄዎች ተቀብሎ ከመነሻ ውሳኔ ሀሳብ ጋር ለቦርድ ያቀርባል፤
- በተጭበረበረ ማስረጃ ወይም ሀሰተኛ ሠነድ የይቅርታ ተጠቃሚ ሆነዋል ወይም ቅድመ ሁኔታ ተጥሷል የሚል አቤቱታ ሲቀርብ ተቀብሎ መረጃዎችን ያሰባስባል፤ ይመረምራል፤ ትክክል ሆኖ ሲገኝም የተሰጠው ይቅርታ እንዲሰረዝ ከመነሻ ውሳኔ ሀሳብ ጋር ለቦርዱ ያቀርባል፤
- በይቅርታ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት እና በአፈፃፀሙ ዙሪያ በይቅርታ ሥራው ላይ ለሚሳተፉ አካላት እና ለሕግ ታራሚዎች የግንዛቤ ማጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፤
- የሞት ፍርደኞችን መረጃ አጠናቅሮ በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት እንዲላክ ማድረግ እና ቅጣቱ እንዲፈፀም ሲወሰን ከማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
- በአዋጅ፣ በደንብና በመመሪያው መሠረት ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የሕግ ታራሚዎች በመለየት በልዩ ሁኔታ በይቅርታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከመነሻ ውሳኔ ሃሳብ ጋር ለቦርድ ማቅረብና ውሳኔውን ማስፈፀም፤
- የይቅርታ ተጠቃሚ ሆነው ወደህብረተሰቡ ውስጥ የተቀላቀሉ የሕግ ታራሚዎች በሰላም እየኖሩ ስለመሆናቸው እና ዳግም ወደ ወንጀል ስላለመግባታቸው ጥናት ማድረግ እና የጥናቱን ውጤት መተግበር፤
- የይቅርታ ተጠቃሚ ሆነው ወደህብረተሰቡ ውስጥ የተቀላቀሉ የሕግ ታራሚዎች በሰላም እየኖሩ ስለመሆናቸው እና ዳግም ወደ ወንጀል ስላለመግባታቸው ጥናት ማድረግ እና የጥናቱን ውጤት መተግበር፤