በጤናው ዘርፍ ጥራትና ደህንነት በማረጋገጥ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ
Seble
Fri, 07/04/2025 - 17:14
በጤናው ዘርፍ ጥራትና ደህንነት በማረጋገጥ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተመላከተ
(ሆሳዕና፣ሰኔ 27/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አመታዊ ስራ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶችና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ እንደገለጹት የጤና ቁጥጥር ስራ ዋነኛ አላማ ህብረተሰቡ በጤናው መስክ የሚያገኛቸው አገልግሎቶች ጥራታቸው እና ደህንነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን እና የተቀመጠላቸውን ደረጃ እንዲያሟሉ መቆጣጠር እና ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲኖር ማስቻል ነው ብለዋል።