Tue, 10/22/2024 - 18:37
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት ጋር የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
ቢሮው ከተጠሪ ተቋማትና ከስር መዋቅሮች ጋር በሀላባ ከተማ የ2016 የማጠቃለያ አፈፃፀም ግምገማ ላይ የተገኙት የቢሮ ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን በንግግራቸዉ ክልላችን በአዲስ መልክ በተዋቀረ ቢሆንም የህግ የበላይነት እንዲከበር ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ገደብ የጣሰ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚረጩት የጥላቻ እና ሀሰተኛ ወሬ የሚያሰራጩ በአብዛኛው አደብ እንዲገዙ የተደረገበት የሚጠቀስ ሲሆን በክልላችን ዘላቂና አስተማማኝ ሠላም እንድሰፋፋ ከፍትህ ሴክተር የሚጠበቀዉን ቀልጣፋ ፥ ፍትሃዊ ፥ ተደራሽ እና ተአማኒነት ያለው አገልግሎት መስጠት ይጠበቅብናል ሲሉ በንግግራቸው ገልፀዋል።
በመቀጠልም የ2016 በጀት አመት ዕቅድ ሪፖርት የቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት በል/ዕ/ኢኮ/ሚ አስ/ር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ፍቅሩ የቀረበ ሲሆን የታችኛው መዋቅር ክትትልና ድጋፍ ሪፖርት እና የዐቃቤያን ህግ መዝገቦችየ ኦዲት ሪፖርትም በባለሙያዎች የቀረበ ሲሆን በመድረኩም የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በተነሱ ጉዳዮችም ዙሪያ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ምላሽ አሰተያየት እና የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።
ዘገባዉ፤ የፍትህ ቢሮ መንግስት ኮሙኒኬሽን
Image
