Skip to main content
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ468 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻዉ ጣሰው የዘንድሮዉን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ የክልሉ መንግስት ለ468 የህግ ታራሚዎች የክልሉ መንግሥት ይቅርታ ማድረጉን ተናግረዋል።
ርዕሰ-መስተዳደሩ በወንጀል ጉዳይ እስራት ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት እየታረሙ ከሚገኙ ታራሚዎች ውስጥ ህጉ የሚጠይቀውን መስፈርት አሟልተው ለተገኙ በመደበኛ ቅድመ ሁኔታ ወንድ 453 ሴት 8 በድምሩ ለ461 ታራሚዎች እና በልዩ ሁኔታ ደግሞ ወንድ 4 ሴት 3 በድምሩ ለ 7
በአጠቃላይ ለ468 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ እንደተደረገላቸው ጠቁመዋል።
ይቅርታ ከተደረገላቸዉ ታራሚዎች መካከል 463ቱ በሙሉ ይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ የተወሰነ ሲሆን ከእነሡ መካከልም 453ቱ ወንዶች፣ 10 ሴቶች መሆናቸዉ ተገልጿል ።
በሌላ በኩል 4 ወንድ እና 1 ሴት ታራሚዎች የእስራት ፍርድ ጊዜ እንዲቀነስላቸው ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡
ክቡር ርዕስ-መስተዳደሩ ባስተላለፉት መልዕክት ይቅርታ ተጠቃሚዎች በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ በመልካም ስነምግባራቸው ምሳሌ በመሆን ህብረሰተሰቡን እንዲክሱ አሳስበዋል ።
ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ-ታራሚዎች በማረሚያ ቆይታቸው ወቅት በቂ ትምህርት የተሰጣቸው እና በፈፀሙት የወንጀል ተግባር የተፀፀቱና የታነጹ ስለመሆናቸው ስለተረጋገጠ ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ ተገቢውን ድጋፍ እድያደርግላቸውም ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።
ምንጭ፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ መ/ኮ
Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ468 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ