Skip to main content
  1. የህግ ኦዲትና እንስፔክሽን እና ቅሬታ ማስተናገጃ ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
  •   በወንጀልና በፍትሐብሔር መዝገብ ላይ የተሰጡ የማቋረጥ ወይም የመዝጋት ውሳኔዎችን ሕጋዊነትና አግባብነት ምክንያት ቅሬታው ለቢሮ ኃላፊ ሲቀርብ መመርመርና የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣
  •   በክልል ማዕከል ጀምሮ እስከ ስር መዋቅር ወደ ፍ/ቤት የቀረቡ ክሶች በሕግ አግባብ የቀረቡ መሆኑን በታቀደ ወይም ድንገተኛ የሕግ ኦዲት ሥራ ማረጋገጥና ዉጤቱን ለዋና ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቅርቦ በሚያግባባ ጉዳይ ግብረ መልስ ይሰጣል፣
  •   ጥቆማን ወይም የበላይ አመራር ትዕዛዝን መነሻ በማድረግ ማንኛዉንም የዓቃቤ ሕግ ውሳኔዎችን ሕጋዊነት በኦዲትና ኢንስፔክሽን ያጣራል፣
  •   ዐቃቢያነ ሕግ በተቋሙ የወጡ መመሪያዎችንና የተዘረጉ አሰራሮችን ጠብቀዉ እየሰሩ መሆኑን ያረጋግጣል፣
  •  በኦዲት ግኝቶች ላይ ተመስርቶ ግብረ መልስና ማስተካከያ እንዲደረግ ለኦዲት ተደራጊዉ የሥራ ክፍል መላክና የበላይ አመራሩ እንዲያውቀው ማድረግ፣አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣
  •   የኦዲት ግኝትን መሰረት በማድረግ አስፈላጊዉን የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፣ 
  •   ከሥነ-ምግባር ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመቀበል አጣርቶ ለበላይ አመራር የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፣ 
  •   በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚቀርቡ ማንኛዉንም ቅሬታዎች ተቀብሎ በሚመለከተዉ ክፍል እንዲጣሩ ወይም እንዲፈቱ ይልካል፣
  •   ለዳይሬክቶሬቱ የተላኩ አቤቱታዎች/ቅሬታዎች በወቅቱ ምላሽ ስለማግኘታቸዉ መከታተል፣ ተገልጋዮች በዜጎች ቻርተር መሰረት አገልግሎት እያገኙ መሆን አለመሆኑን መከታተልና በተቋሙ ያለውን የተገልጋዮችን የእርካታን ደረጃ በጥናት ይለያል፣ 
  •   የሥራ ክፍሎች በተቀመጠው የተቋሙ አሰራርና ሕግ መሰረት አገልግሎት ስለመስጠታቸው ማረጋገጥ እና የቅሬታ ምንጮችን በጥናት በመለየት የመፍትሔ ሀሳብ ያቀርባል፣