Skip to main content
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ክላስተር የሚገኙ የክልሉ ተቋማት አባላት "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት'' በሚል መሪ ሀሳብ የ4ኛ ዙር የአባላት ስልጠና ማካሄድ ጀምሯል።
ጥቅምት፣26/2017ዓ.ም
"የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት'' በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ የተጀመረው የ4ኛ ዙር ስልጠና በሀላባ ቁልቶ ማዕከል የሚገኙ የክልል ተቋም አባል ስልጠና እየተሰጠ ሲሆን በንድፈ ሀሳብና በነባራዊ እውነታዎች ተደግፎ በሚሰጠው በዚህ ስልጠና በየደረጃው ያለው ባለሙያ ሀገራዊ ፣ቀጠናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ ወቅቱን የዋጀና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል።
ስልጠናው ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ አባሉ በአሰተሰሰብ ፣ በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ ምግባር ጎልብቶ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃትና በቁርጠኝነት ለመወጣት የሚያስችለውን አቅም ያዳብራል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ :ማእከላዊ ኢት. ብልፅግና
Image
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ክላስተር የሚገኙ የክልሉ ተቋማት አባላት "የህልም ጉልበት ለእመርታዊ እድገት'' በሚል መሪ ሀሳብ የ4ኛ ዙር የአባላት ስልጠና ማካሄድ ጀምሯል።