Tue, 12/24/2024 - 17:46
የፍትህ ተቋማት የለውጥ ትግበራ በማሳለጥ ቀልጣፋና ፈጣን ፍትህ ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
ህዳር 4/2017) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የዳኝነት እና የፍትህ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የተዘጋጀ የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ህብረተሰቡ በፍትህ ስርአቱ ላይ አመኔታ እንዲኖረው ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዉ
:በፍርድ ቤቶች እና በፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ላይ የሚስተዋለው መሰረታዊ ችግር እንዲፈታ መስራት ይገባል ብለዋል።
ከክልል ጀምሮ ያለውን የፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ተቋማት ላይ የሚስተዋለውን የአሰራር ጥሰት በማሻሻል የህዝቡን የፍትህ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል። ህዝቡ በተቋማት ላይ እምነት እንዲያጣ ያደረጉ ምክንያቶችን መፈተሽ አብይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም አፈ ጉባኤዋ አስረድተዋል።
የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥባቸው ዘርፎች ላይ የትራፊክ ፖሊሶች የስነ ምግባር ብልሽት የህዝቡ የቅሬታ ምንጭ መሆኑንም አብራርተዋል። ከዳኝነት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ስራቸውን በታማኝነት የሚያከናውኑ ዳኞች የመኖራቸውን የተናገሩት አፈ ጉባኤዋ የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸው ዳኞች ስለመኖራቸውም ጠቁመዋል ።
በአካባቢ፣በጎሳ፣በገንዘብ በሀይማኖት እና ተዛማጅ ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ የሚስተዋሉ የፍትህ ስርአት መጓደል ችግሮችን መፍታት እንደሚገባም ዋና አፈ ጉባኤዋ አሳስበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እንደገለጹት የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የለውጥ ትግበራው በፍትህ ተቋማት የሚስተዋለውን የአገልግሎት ጥራት መጓደል እና የሥነ-ምግባር ችግር በመቅረፍ በተገልጋይ ህብረተሰብ ዘንድ የሚነሱ የቅሬታዎችን ለመፍታት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ሁሉ በዲሞክራሲ፣በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ የላቀ ሚና አላቸው ብለዋል።
የፍትህ ተቋማት ለህዝቡ የሚሰጡትን አገልግሎት በገለልተኛነት በፍትሀዊነት እና ተአማኒነትን መሰረት ባደረገ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አብራርተዋል። ከፖሊስ፣ከዳኞች እንዲሁም ከአቃቤ ህግ አንጻር የሚስተዋሉ የስነ ምግባር ችግሮችን ለመለየት ተከታታይ ህዝባዊ ውይይት በማካሔድ እንደሚገባም አቶ አንተነህ ተናግረዋል ።
የተጠያቂነት አሰራር በመተግበር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅም ኃላፊው አሳስበዋል። ባለፈው በጀት አመት ክልሉን ለማተራመስ የተከፈቱ ሀሰተኛ ማህበራዊ ትስስር ሚዲያዎች ላይ ክትትል በማድረግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም የጥላቻ ንግግር በሚያሰራጩ አካላት ላይ ተገቢውን እርምጃ መውሰድ ተገቢ ስለመሆኑም አቶ አንተነህ አብራርተዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት የፍትህ ዘርፍ ተቋማት የለውጥ ትግበራው በፍትህ ተቋማት የሚስተዋለውን የአገልግሎት ጥራት መጓደል እና የሥነ-ምግባር ችግር በመቅረፍ በተገልጋይ ህብረተሰብ ዘንድ የሚነሱ የቅሬታዎችን ለመፍታት የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ገለፀዉ።
ባለፉት አመታት ከማዳበሪያ እዳ አመላለስ ጋር ተያይዞ የተሰሩ ስራዎች በፍትህ ሴክተሩ የተቀናጀ ስራ መሆኑንም አቶ ኡስማን ተናግረዋል። የተወረሩ የወል መሬቶችን ስርዓት ማስያዝ ለሰዎች እና ለእእስሳት ህይወት የጤና ጠንቅ የሆኑ ህገወጥ መድሀኒት ቁጥጥር ላይ በትብብር መስራት እንደሚገባም ሀላፊው ጠቁመዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እንደገለጹት የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር መጎልበት በዘርሩ የሚካሔደውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል።
በክልሉ ሰላምን ልማትን እና ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አቶ ኤርሲኖ በንግግራቸው አመላክተዋል:: ዳኞች ገለልተኛ ሆነው ለህዝብ የሚሰጡትን አገልግሎት በተገቢው መንገድ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የምድብ ችሎት ተደራሽነትን በማስፋፋት ህብረተሰቡ ከምርት ተግባሩ ሳይነጠል አገልግሎት የሚያገኝበትን ስርዓት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል።
በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ :የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ : በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ጨምሮ የፍትህ ዘርፍ የክልልና የዞን መዋቅር አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት መድረክ ተጠናቀ ቀ::
ለፍትህቢሮ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ዘገበ:
ሰላማዊት ጴጥሮስ
Image
