የማዕከላዊ #ኢትዮጵያ ክልል #ርዕሰ መስተዳድር #እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሰኔ ወር ያከናወኗቸው #አበይት ጉዳዮች
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በተያዘው በጀት ዓመት በሆሳዕና ከተማ ግንባታቸው እየተካሔደ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አድርገዋል።
በከተማው በመገንባት ላይ የሚገኙ የክልል ተቋማት የቢሮ ግንባታ ሂደት ርዕሰ መስተዳድሩ ምልከታ አድርገዋል።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)ለትምህርት ሚኒስትሩ ለብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በጽ/ቤታቸው አቀባበል ያደረጉት ባሳለፍነው የሰኔ ወር ነበር።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችን ተመልክተዋል።
.........................................//.......................................ርዕሰ መስተዳድሩ በሆሳዕና ከተማ በዋቸሞ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ6ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስጀምረዋል።
በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ማሻሻያ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው( ዶ/ር ) የሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ አሁናዊ የአፈፃፀም ሁኔታን በጽህፈት ቤታቸው ገመገሙ ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋም የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረት ስራ ልማት ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር መርቀው የከፈቱት በመገባደድ ላይ በሚገኘው ሰኔ ወር ነበር
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር )የክልሉን አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ገምግመዋል
ርዕሰ መስተዳድሩ ከጸጥታ አመራሮች ጋር የክልሉን አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታ በጽ/ቤታቸው ገምግመዋል።
በክልሉ ህዝቡን ያሳተፈ ዘላቂ ሰላም እውን በማድረግ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
.........................................//.......................................
አርሶ አደሩ የሚያቀርበው ምርት ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በቀጥታ ወደ ሸማቹ ማህበረሰብ እንዲደርስ የግብይት ማዕከላትን ማዘመን ተገቢ ነው -ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)በሆሳዕና ከተማ ከሰንበት እስከ ሰንበት ዘመናዊ የግብይት ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እንደገለፁት የሰንበት ገበያ ካለው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አንጻር አድማሱን በማስፋት ሳምንቱን ሙሉ ከሰንበት እስከ ሰንበት አገልግሎት መስጠት እንዲችል አዲስ ኢኒሼቲቭ በማስጀመር ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በዋቸሞ ትምህርት ቤት የ6ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና አስጀምረዋል።
.........................................//.......................................
የማረቆ ልዩ ወረዳ የልማት ኮሪደር እንዲሆን በልዩ ትኩረት እንሰራለን - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ የገራድ ቢመዶ አጠቃላይ ሆስፒታል የግንባታ ስራ አስጀምረዋል
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የማረቆ ልዩ ወረዳ የልማት ኮሪደር እንዲሆን በልዩ ትኩረት እንሰራለን ያሉት ባሳለፍነው ወር ነበር።
የማረቆ ህዝብ የጀመረው የልማት እና የትብብር እሴት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ከጋምቤላ ክልል ከመጡ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)በጋምቤላ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ በአቶ አሽኔ አስቲን ከተመራ ልኡካን ቡድን ጋር በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው
ርዕሰ መስተዳድሩ ከልኡካን ቡድኑ ጋር በነበራቸው የውይይት መድረክ እንደገለጹት ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ በአጭር ጊዜ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመዋል።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራ በጽ/ቤታቸው ገመገሙ
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጽ/ቤታቸው ገምግመዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ ዲጂታላይዝ ስርዓት በመዘርጋት ተወዳዳሪነትን ማሳደግ እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።
.........................................//.......................................
የተማሪዎችን የፈተና ውጤት ለማሳደግ የቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ ትኩረት ተደርጓል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ምልከታ አድርገዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) እንደገለጹት በክልሉ በዛሬው እለት እየተሰጠ ያለውን የ8ኛ ክፍል የፈተና ሂደት አስመልክቶ በምስራቅ ጉራጌ እና በስልጤ ዞን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ምልከታ አድርገዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የተማሪዎችን የፈተና ውጤት ለማሳደግ የቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
.........................................//.......................................
በክልሉ የሚገነባው የገጠር ኮሪደር ልማት በፍጥነትና በጥራት ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር )
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆኑ ሞዴል የገጠር መንደሮች የግንባታ ስራን ሂደት ምልከታ አደረጉ።
በክልሉ የሚገነቡ የገጠር ኮሪደር ልማት በፍጥነትና በጥራት እንዲፈፀም በቁርጠኝነት እየተመራ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
....................................//..................................
የጉራጌ ህዝብ ባህልና ቋንቋን በጋራ ለማሳደግ የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
የጉራጌና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች በጋራ ያዘጋጁት የጉራጌ ህዝብ ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚየም በተለያዩ ዝግጅቶች በወልቂጤ ከተማ ተከብሯል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) የጉራጌ ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሲምፖዚምን መርቀው ከፍተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት የጉራጌን ህዝብ ባህል፣ታሪክ እና ቋንቋን ለማሳደግ የሚደረገው ርብርብ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
...................................//...................................
የፅዳትና አረንጓዴ አሻራ ስራዎችን ተከታታይነት ባለው መልኩ መተግበር ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
የሁለተኛው ዙር ክልል አቀፍ የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት የቆሻሻ አወጋገድ ቁጥጥር ስርዓት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
..................................//....................................
በተቀናጀ ግብርና የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መረባረብ ያስፈልጋል፦ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
በክልሉ ግብርና ቢሮ '' የግብርና ሴክተር ምሰሶዎችን በማሳካት የበለፀገ ቤተሰብ ለማየት እተጋለሁ'' በሚል መሪ ቃል በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲና በዱራሜ ካምፓስ ለግብርና ልማት ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) በስልጠናው ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የተለያዩ የልማት ስራዎችን በመስራት ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
...............................//.....................................
ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ለዜጎች ፍትሃዊና ተደራሽ ልማት ማረጋገጥ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) በተገኙበት የመንግስት እና የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች የጋራ ፎረም ተመሰረተ።
በዚሁ ፍቅር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ችግር ፈቺ ፕሮጀክትን በመቅረፅ ለዜጎች ፍትሃዊና ተደራሽ ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር ) ተናግረዋል።
.................................//.....................................
በክልሉ ከተሞች የተያዙ የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳድሩ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በክልሉ እየተካሄዱ ያሉ የከተማ ልማት ኢንሼቲቮችን ወቅታዊ ሁኔታ ገምግመዋል።
በክልሉ ከተሞች የተያዙ ሀገር አቀፍና ክልላዊ የልማት ፕሮጀክቶችንና ኢንሼቲቮችን በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በልዩ ትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተናግረዋል።
.................................//.....................................
ምቹ የመፈተኛ ማዕከላትን በማዘጋጀት ረገድ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለተማሪዎች ሰላማዊና ምቹ የመማሪያ ማዕከላትን በማዘጋጀት ረገድ ውጤታማ ሥራ ተከናውኗል አሉ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የቅድመ ዝግጅት ስራ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል።
የመምህራንን አቅም ማሳደግ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው አስታውሰው፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እና በሞዴል ፈተናዎች በቂ ልምምድ እንዲያደርጉ መሰራቱን ተናግረዋል።
.................................//.....................................
በክልሉ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለ1ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር )
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሞዴል ኢንተርፕራይዞች እውቅና ፣ደረጃ ሽግግር እና የማትጊያ መርሐ ግብር በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) በመድረኩ ማጠቃለያ በሰጡት የስራ መመሪያ እንደገለጹት በቀጣይ ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ ከ9 ነጥብ 15 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዷል።
በክልሉ በ2017፣በ2018 እንዲሁም በ2019 በጀት ዓመትለ1ነጥብ 2 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጠር ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
.................................//.....................................
20ኛው የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በህዝቦች መካከል የላቀ መስተጋብር እንዲፈጠር ያስችላል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ላይ ምክክር አካሂደዋል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) በምክክር መድረኩ እንደገለጹት በክልሉ በዓሉን ደማቅ በሆነ መልኩ ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተግባር መግባት ተችሏል ብለዋል።
