Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ 2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ መንፈቅ አመት የስር መዋቅር የOቃቤ ህግ የድጋፍ ክትትል ሪፖርት ገመገመ።

####################

(ሀላባ ፣ ሰኔ 30/ 2017)  የክልሉ ፍትህ ቢሮ ከቢሮው ማኔጅመንት አካላት ጋር የበጀት ዓመቱን የ0ቃቤ ህግ የድጋፍ ክትትል ሪፖርት ግምገማ አካሄደ። ቢሮው የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እና ተልዕኮውን መሠረት ያደረገ የ 7 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ በማዘጋጃት  የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ጥንካሬ እና ድክመት በመገምገም የ 2017 በጀት ዕቅድ ተዘጋጅቶ ባለፉት 12 ወራት ሲተገበር ቆይቷል።

በዚህም መሠረት ቢሮው በዕቅድ የያዛቸው የቁልፍ እና የተልዕኮ ተኮር ተግባራት በዞን ፍትህ መምሪያዎችና በልዩ ወረዳ ፍትህ ጽ/ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ዙሪያ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርጉ አራት አራት አባላት ያሉት ሁለት ቡድኖች በ7ዞኖችና በ3 ልዩ ወረዳዎች በማሠማራት ለተቋማቱ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እና በቼክ -ሊስት በተቀመጠው የምዘና መሥፈርት መሠረት ድጋፍና ክትትላቸውን ሪፖርት አጠቃላይ ለተቋሙ ማንጅመንት አባላት የድጋፍ ክትትሉን ግብረ መልስ በማቅረብ በተቋማቱ የሚታዩ ጥንካሬዎች በ2018 በጀት ዓመት የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ክፍተቶች ደግሞ በቀጣይ እንዲታረሙ ትኩረት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ግምገማውን አከናውኗል።
የቢሮው መ/ኮ

Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ 2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ መንፈቅ አመት የስር መዋቅር የOቃቤ ህግ የድጋፍ ክትትል ሪፖርት ገመገመ።