የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ብሄራዊ ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀመሩ ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ለተማሪዎቹ መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እና ሌሎችም ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ እንደገለጹት በዚህ ዙር 22 ሺ108 ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 3,584 በኦንላይን 18, 524 የሚሆኑት ደግሞ በወረቀት ሶስት ዩኒቨርስቲዎችን ጨምሮ በ9 የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናቸውን እየወሰዱ ይገኛሉ ።
ምንጭ፦ የክልሉ መ/ ኮ
