የጠበቆች፣ ሲቪክ ማህበራትና ሰነድ ምዝገባ ዳይሬክቶረት
የዳይሬክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
- በቢሮው ማቋቋሚያ አዋጅ 03/2016 አንቀጽ 5/8/ከሀ-በ የተሰጡትን ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ስራ ላይ ያዉላል፡፡
- በክልሉ ፍርድ ቤቶች መቆም ለሚፈልጉና ለጥብቅና ፌቃድ ፈተና መፈተን ለሚያስፈልጋቸዉ የሙያ ብቃትና ስነምግባር ሲያሟሉ በፈተና የጥብቅና ፈቃድ መስጠት፣
- በክልሉ በማናቸውም ፍርድ ቤት መቆም ለሚችሉ ጠበቆች የሙያ ብቃትና ስነምግባር ሲያሟለ ያለ ፈተና የጥብቅና ፈቃድ መስጠት፣
- የሙያ ግዴታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ጠበቆች በየዓመቱ የጥብቅና ፈቃድ ማደስ፣
- ጠበቆች የገንዘብ አቅም የሌላቸዉ የህብረተሰብ ክፍልች ነፃ የህግ ምክርና የጥብቅና አገልግልት እንዲሰጡ ማድረግ፣
- ምትክ የጥብቅና ፈቃድ መታወቂያ ደብተር መስጠት፣ አስፈላጊ መስፈርት ሲሟላ የጥብቅና ፈቃድን በአደራ ማስቀመጥና መመለስ፣
- የሕግ ጉዳይ ጸሀፊዎች እና የጠበቃ ረዳቶች ይመዝገቡልኝ ጥያቄ ተቀብሎ መመዝገብና ማሳወቅ፣
- ከዳይሬክቶቱ ፈቃድ የተሰጣቸው ጠበቆች የሙያና የሥነ-ምግባር ግዴታቸውን የመወጣትና የሥነ-ምግባር ደንቡንና አግባብ ያላቸውን ሌሎች ሕጎች በማክበር መስራታቸውን ለማረጋገጥ ተገቢውን ክትትል፤ ቁጥጥርና ድጋፍ ማድረግ፣ የዲስፕሊን ክስ ማቅረብና አቤቱታ ተቀብል ለዲስፒልን ጉባዔ አቅርቦ ማስወሰንና ማስፈፀም ናቸው፣
- በዞን፣ በልዩ ወረዳ፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ያሉ የጠበቆች፣ ሲቪል ማህበራት እና ሰነድ ምዝገባ ስራ አሰራር ይከታተላል ተገቢዉን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል፤
- ሌሎች ከስራዉ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉን ተግባራት ያከናዉናል፡፡