Skip to main content

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው ውሳኔ የተሰጠበትን ድንጋጌ አርሞ አፀደቀ

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው ውሳኔ የተሰጠበትን ድንጋጌ አርሞ አፀደቀ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 30 ፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ ልዩ ስብሰባው፤ በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 49 (2)ሀ መሠረት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም በሚል ከሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው፤ ከአሁን በፊት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አርሞ አፅድቋል፡፡

ለሰብአዊ መብት ጥሰት በር ይከፍታል የተባለው የአዋጅ ድንጋጌ ተሻሻለ

ለሰብአዊ መብት ጥሰት በር ይከፍታል የተባለው የአዋጅ ድንጋጌ ተሻሻለ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ ልዩ ስብሰባው፤ በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 49 (2)ሀ መሠረት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም በሚል ከሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው፤ ከአሁን በፊት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አርሞ አፅድቋል፡፡

የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 37ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፤ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1387/2017 አድርጎ ማፅደቁ አስታውሰዋል፡፡

በ2017 በጀት አመት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።

በ2017 በጀት አመት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።

(ሆሳዕና፣ ሰኔ 30/2017) ፣ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ከነገ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ግብራቸውን እንዲከፍሉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

በ2017 በጀት አመት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው እንዳለው በበጀት አመቱ 20 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ  ከተለያዩ የገቢ አርእስቶች ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ አሁን ባለው ሂደት 16 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።

የቢሮው ሃላፊ ተወካይና የደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ሃላፊ  አቶ ደግፌ መለሰ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የክልሉ መንግስት ወጪን በሚሰበሰብ ገቢ ለመተካት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የገቢ አማራጮችን ለማስፋት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

የትጋት ምሳሌ ከመሆን እስከ እርቅ አባትነት ስማቸው የሚነሳው የሰላም አባት ሀጂ ከድር

የትጋት ምሳሌ ከመሆን እስከ እርቅ አባትነት ስማቸው የሚነሳው የሰላም አባት ሀጂ ከድር 
 

ሀጂ ከድር ተካ  አርሶ አደርና የሀገር ሽማግሌ ናቸው። በባህላዊ ዳኝነት ሥራቸው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ሀጂ ከድር ተካ ዛሬም አንቱታን ያተረፉባቸውን አያሌ ሥራዎች እየሰሩ ይገኛሉ።

ሀጂ በ80ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ናቸው። ውልደታቸውና ዕድገታቸው በስልጤ ዞን፣ ሳንኩራ ወረዳ፣ ዓለም ገበያ ውስጥ ነው።

ሀጂ ከድር ተካ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የተራራቁትን በማቀራረብ በብዙዎች ዘንድ የተመሰከረላቸው አርሶ አደርና የሀገር ሽማግሌም ናቸው።

ገና በወጣትነት የዕድሜ ክልል እያሉ የቀበሌ አስተዳደርና ሚሊሻ ሆነው የሳንኩራን ህዝብ በቅንነት ማገልገላቸውን ብዙዎች ይመሰክራሉ።

ሀጂ ከድር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመቀበልና በመተግበር ረገድ ግንባር ቀደም ከሚባሉ አርሶ አደሮች መካከል ናቸው።

የማዕከላዊ #ኢትዮጵያ ክልል #ርዕሰ መስተዳድር #እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሰኔ ወር ያከናወኗቸው #አበይት ጉዳዮች

የማዕከላዊ #ኢትዮጵያ ክልል #ርዕሰ መስተዳድር #እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሰኔ ወር ያከናወኗቸው #አበይት ጉዳዮች

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በተያዘው በጀት ዓመት በሆሳዕና ከተማ ግንባታቸው እየተካሔደ የሚገኙ  የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አድርገዋል።

በከተማው በመገንባት ላይ የሚገኙ የክልል ተቋማት የቢሮ ግንባታ ሂደት ርዕሰ መስተዳድሩ ምልከታ አድርገዋል።
.........................................//....................................... 
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)ለትምህርት ሚኒስትሩ  ለብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በጽ/ቤታቸው አቀባበል ያደረጉት ባሳለፍነው የሰኔ ወር ነበር።

ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችን ተመልክተዋል።

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ግንባታ

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ግንባታ 
የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነስ  የአምራቹንና ሸማቹን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተግባር መሆኑን  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ

(ሆሳዕና ፣ሰኔ 27/2017) ቢሮው  በዱራሜ ከተማ ለሚገነባው  ከሰንበት እስከ ሰንበት ዘመናዊ የግብይት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የማኖር መርሐ ግብር አካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ እንደገለፁት  
የሰንበት ገበያ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በህገወጥ ነጋዴዎች ሳይበዘበዙ  ኑሮ ውድነትን ለማቃለል ሳምንቱን በሙሉ የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ብሎም አርሶ አደሩን ከሸማቹ ጋር  በቀጥታ በማገናኘት  የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ተግባር እንደሆነም ገልፀዋል።