Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።

(ሃምሌ 3/2017)፣ በተሻሻለው አዲሱ አማራጭ የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ መመሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች በዱራሜ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አምሪያ ሲራጅ ስልጠናውን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ቢሮው የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተፈጥሮአዊ እና ሰውሰራሽ አደጋዎች ለተጋለጡ ህጻናት በማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ወይዘሮ አምሪያ ባልተደራጀ መንገድ ሲሰጥ የነበረውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የተደራጀና ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጣ መልኩ መፈጸም ማስቻል የስልጠናው አላማ መሆኑን ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ አማራጭ የድጋፍና እንክብካቤ መመሪያ መዘጋጀቱን የገለጹት ምክትል የቢሮ ኃላፊዋ መመሪያው ተጠያቂነትን ማስፈን ያስችላል ብለዋል።

በተሻሻለው አዲሱ አማራጭ የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ መመሪያ ላይ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ወጥ አረዳድ ፈጥረው ለተግባራዊነቱ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

ቢሮው ከሆልት ኢንተርናሽናል ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠናውን እየተሰጠ ሲሆን
የቢሮው የስራ ኃላፊዎችና በየደረጃው የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

ምንጭ፡ የክልሉ መ/ኮ

Image
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።