በክልሉ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)
(ሆሳዕና፣ሐምሌ 7/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር )ከዞኖችና ከልዩ ወረዳ አመራሮች ጋር በጽ/ቤታቸው እየመከሩ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር በምክክር መድረኩ እንደገለጹት የክልሉን መንግስት የ2017 በጀት አመት አፈጻጸም አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት ይካሔዳል ብለዋል።
በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ስራዎች ሪፖርት፣የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ፣የ5 ሚሊየን ኮደርስ፣የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እና በሌሎችም አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር የሚያስችል መድረክ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ስራዎችን በቅንጅት እና በትብብር የተመራበት ሂደት፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ በማድረግ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ምክክር እንደሚደረግም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
የህዝብ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አንጻር የተከናወኑ ተግባራት እንዲሁም አመራሩ ህብረተሰቡን እና ሰራተኛውን አስተባብሮ ሙሉ ጊዜውን በስራ ላይ ስለማዋሉ ውይይት እንደሚደረግ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
የመንግስትን ፖሊሲ ከማሳካት አንጻር የአመራሩ ቁርጠኝነት፣የተመዘገቡ ውጤቶች፣መልካም ተሞክሮዎች እንዲሁም በጉድለት የተለዩ ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚገባም አመላክተዋል።
በመድረኩ የዞኖች፣የልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪዎችና አስተባባሪ አካላት ተገኝተዋል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
