የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላት የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
(ሆሳዕና፦ሀምሌ 7/2017) በምክር ቤቱ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸምን በወልቂጤ ከተማ ገምግሟል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ሰው ተኮር ተግባራት የሚያበረታታ እንደሆነም ገልፀዋል።
የህብረተሰቡን ኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የተጀመረው የሰንበት ገበያ ስራን በማጠናከር አቅራቢውን እና ሸማቹን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ በመሆኑ ለጥራቱ በልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ነው ያሉት።
እንዲሁም የሰንበት ገበያን ምርት አቀራረብ ላይ ለሸማቹ እጥረት እንዳይኖር የተሻለ አሰራርን ዘርግቶ አጠናክሮ እንዲሰሩም አሳስበዋል።
ከነዳጅ ምርት አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታዩ ጉድለቶችን በቀጣይ ለመስተካከል ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር ያስፈልጋል።
ህገ ወጥ አሰራርን ለመከላከል እና የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እየተሰራ ያሉ ተግባራት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገልፀዋል።
የፍጆታ ምርቶችን ለህብረተሰቡ ከማቅረብ አኳያ የተሰሩ ስራዎች አበራታች ቢሆን እጥረት እንዳይኖር ክትትል ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ከህዝብ ተጠቃሚነት አንጻር በቢሮ ደረጃ በርከታ ስራዎች መሰራቱን በመግለፅ የተጀመሩ የግብይት ማዕከላት ግንባታ አገልግሎት እንዲሰጥ መረባረብ ያስፈልጋል ተብሏል።
ቢሮው በአመቱ ያቀዳቸውን ዕቅድ ለማከናወን የተንቀሳቀሰበት ሂደት የሚያበረታታ እና አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ የተቻለበት እንደሆነ በመግለጽ በቀጣይም የቅንጅት አሰራሮች ሊጠናከር ይገባል ሲሉ አቶ ታመነ ገልፀዋል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
