Skip to main content

በክልሉ ላቦራቶሪን በማደራጀት በማስመረቅ የምርመራ አገልግሎቶችን በማስጀመርና በማጠናከር ረገድም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተመላከተ።

ሆሳዕና ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት እንድ ክልል አምስት ግቦችን በማስቀመጥ ወደ ስራ መገመቱን ጠቅሰው ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፍን ማፍጠን በሚያስችል መልኩ በርካታ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ከጤና ተቋማት ተደራሽነት አገልግሎት አቅርቦት ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ከማድረስ፣የህብረተሰብን የጤና ሁኔታን ማሻሻል ጥራት ፍትሀዊነት ተደራሽነትን ታሳቢ ያደረገ፣ህብረተሰቡን ከድንገተኛ አደጋዎች የመጠበቅ ስራዎችን ቢሮው በትኩረት መስራቱን ኃላፊው አስታውቀዋል።

አቶ ሳሙኤል ወረዳዎችን ትራንስፎርም ከማድረግ አንጻር በጤና ኤክስቴንሽን  አገልግሎት አሰጣጥና የጤና ስረዓት ምላሽ ሰጪነት መሻሻል ላይ በትኩረት መሰራቱን ጠቅሰው በዚህ ወጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።

በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ መልክ የሚከሰቱ የህብረተሰቡን የጤና አደጋዎች በተለይም ከአየር ሁኔታ ለውጥ፣ ከህዝብ ቁጥር መጨመር፣ከኢንዱስትሪ መስፋፋት፣የአዳዲስ በሽታዎች ክስተት የተፈጥሮ አደጋዎች እና በመሳሰሉት የጤናው ስረዓት በአለም አቀፍ ደረጃ እየተፈተነ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

በዚህም አደጋውን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ ቢሆኑም ማህበረሰባችን ከሚፈልገው የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ጥራት አንጻር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

አቶ ሳሙኤል ክልላችን ከተመሰረተ ጀምሮ በተደረገው እንቅስቃሴ  በጤናው ዘርፍ ስረዓት ለመትከል በተደረገው ጥረት ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

ለአብነትም በክልሉ የሚከሰቱ ወረርሽኞች እንዳይስፉፉ መረጃን የመተንተን አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ  መምጣቱን ጠቁመው በቀጣይ ይበልጥ በማጠናከር ባህል ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ከወባ፣ኮሌራ ወረርሽኝ እና ከምግብና ተያያዥነት ያላቸው ችግሮች ጋር በተያያዘ  በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከህክምናው ጎን ለጎን ህብረተሰቡን የማሳተፉ ተግባር ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

አያይዘውም ከሌሎች ሴክተሮች ጋር የሚደረገው ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በመድረኩ  ባስተላለፉት  መልዕክት እንዳሉት፦

አለም አቀፍ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ጠንካራ የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎቶች፣ ፈጠራዎችና ምርምሮች እንዲሁም ቀልጣፋ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ስርዓት ለድንገተኛ አደጋዎች በምንሰጣቸው የምላሽ አቅማችን ውስጥ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝና እጅግ ከፍተኛ ነው።

ኢንስቲትዩታችን ባሳለፍነው አመት የወረርሽኞችን አሰሳና ቅኝትን ለማጠናከር፣ የማህበረሰብን ግንዛቤ ይበልጥ ለማሻሻል እና ከአጎራባች ክልሎች ጋርም ትብብሮችን ለማጎልበት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በክልሉ የተላላፊ በሽታዎችን ቁጥጥር የአደጋ ቅድመ ዝግጁነትን ማጎልበት፡ አፋጣኝ ምላሾችን መስጠት እንዲሁም የማገገምና ወደ ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ ቄያቸው በመመላስ እንዲሁም የጤና ፍትሃዊነትን በማረጋገጥ ረገድ ከፍተኛ እመርታ አሳይተናል፡፡

የክልሉ ላቦራቶሪን በማደራጀት በማስመረቅ የምርመራ አገልግሎቶችን በማስጀመርና በማጠናከር ረገድም ኢንስቲትዩታችን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል᎓᎓

በመድረኩ ፣የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ዘቢባ ሀጂ ሙሀመድናስ፣የክልሉ መንግስት የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ አቶ ሳሙኤል ገ/ሚካኤል፣የጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፤ከዞንና ከልዩ ወረዳ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በመድረኩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ

Image
በክልሉ ላቦራቶሪን በማደራጀት በማስመረቅ የምርመራ አገልግሎቶችን በማስጀመርና በማጠናከር ረገድም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተመላከተ።