የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ የድረ ገፅ ማስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ቴክኒካል ስልጠና ለቢሮው የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ።
የካቲት 13/2017 ዓ.ም
የቢሮው የድረ-ገጽ ልማት ስራ ተጠናቆ ሆስት https://www.cerjustice.gov.et/ በማድረግ አየር ላይ መዋሉን አስመልክቶ ከማዕ/ኢት/ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በመጡት ከፍተኛ የሶፍትዌር ባለሙያ በሆኑት በአቶ መንሱር ሀምዛ ስለ ዌብ ሳይት ማስተዳደርና በየሳይበር ደህንነት ስልጠና ለቢሮው የስራ ክፍል ኃላፊዎች አጠቃላይ ግለፃእናበተለይም ድረ-ገጹን በቀጣይ ለሚያስተዳድሩ የኢኮቴ እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የማስተዳደርና የሳይበር ደህንነት ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን በቢሮ ም/ኃላፊ እና የወንጀልና የፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ በሆኑት በአቶ ገብሬ አስፋው የመክፍቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን በንግግራቸውም የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ በፍቃደኝነትና በተነሳሽነት ለተደረገልን የተቋሙ ድረ-ገጽ የማበልፀግ እና ባለሙያዎችን የማስልጠን ስራ በቢሮው ስም ላቅ ያል ምስጋና አቅርበዋል። በመቀጥልም በአቶ መንሱር ሀምዛ ስልጠናው በተግባር የተደግፍ ድረ ገፅ የማስተዳድርና የሳይበር ደህንነት ዙሪያ ሠፊ ገለፃ እና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከሰልጣኞቹም የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
