ብሄራዊ ባንክ የንግዱ ማህበረሰብ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳሰበ
ብሄራዊ ባንክ የንግዱ ማህበረሰብ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳሰበ
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 30፣ 2017 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የንግዱ ማህበረሰብ ኢመደበኛ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳሰቡ፡፡
አቶ ማሞ የውጭ ምንዛሪ ገበያ እንቅስቃሴን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ÷ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ አስፈላጊነቱ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ማካሄዱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ይህ የሚሆነውም ባለፈው ዓመት የባንኩ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት መጠን በሶስት እጥፍ በጨመሩ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡
በተጨማሪም ይህ አበረታች ሁኔታ በአዲሱ በጀት ዓመት በመቀጠሉና የማዕከላዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ፍሰትና ግኝት ከተጠበቀው በላይ በማደጉ ነው ብለዋል፡፡
ከውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፊሉን ለባንኮች በጨረታ ማቅረቡ በባንኮች ዘንድ የሚኖረውን የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ከማሳደግ ባለፈ የዋጋንና የውጭ ምንዛሪ ለማረጋጋት ያስችላል ነው ያሉት፡፡
የህዝብ ተወካዮች ከመረጣቸው ህዝብ ጋር የሚያደርጉት ቀጥተኛ ውይይት መንግስትና ህዝብን በማቀራረብ ረገድ የላቀ ሚና አላቸው አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ
የህዝብ ተወካዮች ከመረጣቸው ህዝብ ጋር የሚያደርጉት ቀጥተኛ ውይይት መንግስትና ህዝብን በማቀራረብ ረገድ የላቀ ሚና አላቸው አፈ ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ
(ሐምሌ 29/2017)የክልል እና የፌደራል የፓርላማ አባላት በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ዙር የህዝብ ውክልና ስራ ማከናወን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ እንደገለጹት የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ፓርላሜንታዊ ስርዓትን የሚከተል በመሆኑ ህግ አውጪው፣ህግ አስፈጻሚው እና ህግ ተርጓሚው ተለይተው ሚናቸውን እየተወጡ ነው ብለዋል።
የህግ አውጪው ዋነኛ ተግባር ከሆኑት መካከል የውክልና ስራ ነው ያሉት ዋና አፈ ጉባኤዋ ይህን ተከትሎም የምርጫ አካባቢ ተግባራትን ሲያከናውን የህዝብ ፍላጎትና ጥቅምን በጠበቀና ተጠያቂነትን ባረጋገጠ መልኩ መሆን እንዳለበት አመላክተዋል።
የአረንጓዴዐሻራ- የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ፍትህ ቢሮ አመራሮኛ እና ሠራተኞች ከማለዳ 12:00 ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል ።
(ሀላባ፡ ሀምሌ 24/ 2017) የሰባተኛው አመት ግብ የሆነው ሰባት መቶ ሚሊዮን ችግኞች ተከለ መርሃ ግብር በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ፍትህ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የቀን ውሎ በፎቶ።
የቢሮው መ/ኮ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሀላባ ዞን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስጀመሩ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሀላባ ዞን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስጀመሩ
(ሐምሌ 24/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የአንድ ጀንበር አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እና በእርሳቸው የተመራ ልዑክ ወደ ዌራ ወረዳ ሲደርሱ የአካባቢው ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ነገ ሐምሌ 24/2017 በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሔደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ነገ ሐምሌ 24/2017 በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሔደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ነገ ሐምሌ 24/2017 "በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሔደው " የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ
በአገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደግሞ 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር መትከል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
ይህን ሀገራዊ ጥሪ ከግብ ለማድረስ የክልሉ ህዝብ በነቂስ በመውጣት አሻራውን ማሳረፍ እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተመላከተ
የህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት እንደሚገባቸው ተመላከተ
(ሆሳዕና ፣ሀምሌ 22/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ከሆልት አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበር በተሻሻለው በአዲሱ አማራጭ የህፃናት ድጋፍና ክብካቤ መመሪያ ላይ የተዘጋጀ በሆሳዕና ከተማ እየተሰጠ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አምሪያ ስራጅ እንዳሉት ህፃናት ላይ የሚሰራው ስራ ሀገር ላይ መስራት ነው።
የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ መልኩ በትኩረት መስራት ይገባቸዋል ያሉት ኃላፊዋ በህፃናት ላይ የሚደረገው ድጋፍና ክብካቤ ይበልጥ መጠናከር እንዳለበትም አመላክተዋል።
ከ100 ሺህ ቶን በላይ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋለ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ
ከ100 ሺህ ቶን በላይ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋለ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ
(ሆሳዕና፣ሀምሌ 23/2017)፣ በአዲስ አበባ በዓመት ከመነጨው 100 ሺህ 585 ቶን ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ከአንድ ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገለጹ።
በከተማዋ 325 የመልሶ መጠቀም ማህበራት የተቋቋሙ ሲሆን በዓመት ከተመረተው 983ሺህ 944 ቶን ቆሻሻ 100 ሺህ 585 ቶኑን መልሰው ጥቅም ላይ ማዋላቸውን አስታውቀዋል።
አምስት ሺህ 460 ቶን ቆሻሻን ወደ ኮምፖስት በመቀየር ለከተማዋ የአረንጓዴ ልማት ስራ ማዋል ተችሏል ብለዋል።
እንደ ኢፕድ ዘገባ በጽዳት ዘመቻው 675 ሺህ 384 ነዋሪዎችና ሁለት ሺህ 540 ተቋማት በሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ተሳትፈዋል ።
በዓለም አቀፍ የውል ድርድርና ዝግጅት ዙሪያ ያተኮረ በአይነቱ ልዩ የሆነ ስልጠና ተጀመረ
በዓለም አቀፍ የውል ድርድርና ዝግጅት ዙሪያ ያተኮረ በአይነቱ ልዩ የሆነ ስልጠና ተጀመረ
**********
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልማት ባንክ ግሩፕ /TDB Group/ ጋር በመተባበር በአለም አቀፍ ውል ዝግጅትና ድርድር ሂደቶች ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስራ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ከፌዴራል እና ከክልል ተቋማት የተወከሉ በውል ሂደት ለሚሳተፉ ከ56 በላይ የህግ ባለሙያዎች ከሐምሌ 21 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በሚሰጠው ተግባር ተኮር ስልጠና ላይ በመስኩ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አለምአቀፍ እና የውጭና ሀገር ውስጥ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት ሲሆ፤ ውሎችን በሚገባ በመደራደርና የተቋማትን ጥቅም በተሟላ ሁኔታ የሚያስጠብቁ ስምምነቶችን በማዘጋጀት የህዝብና የመንግስት ጥቅም ለማስጠበቅ አጋዥ የሆነና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት ባለሙያዎች የተሳተፉበት በአይነቱ ልዩ የሆነ የአለምአቀፍ የውል ድርድርና ዝግጅት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያዩ
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መረጃ÷ ከሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ በፊት፣ ወንድሜን አዛሊ አሱማኒ የኮሞሮስ ሕብረት ፕሬዚዳንት ጋር በሁለትዮሽ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።(ኤፍ ኤም ሲ)
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
(ሆሳዕና ፣ሐምሌ 21/2017)2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡
በጉባዔው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በተጨማሪ የጣሊያን ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኒ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼህ መሃሙድ እንዲሁም የኬንያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ተገኝተዋል፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሃመድ፣ የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ፋኦ) ዋና ዳይሬክተር ኩ ዶንግዩ፣ የዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ፕሬዚዳንት አልቫሮ ላሪዮ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና የዩኤንዲፒ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር አሁና ኢዚያኮንዋ፣ በርካታ ሚኒስትሮች እና ባልድርሻ አካላት በጉባዔው እየተሳተፉ ይገኛሉ።