Skip to main content

ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር የሉዓላዊነት ጥቃት አካል ነው - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

(ነሃሴ 6/2017)፣ ኢትዮጵያ ሐሰተኛ መረጃን እና የጥላቻ ንግግርን የብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጥቃት አካል አድርጋ ነው የምትመለከተው ሲሉ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።

ይህን ጥቃት ለማምከን የሚደረገው የተቀናጀ ትግልም በዚያው ልክ ከፍ ያለ ነው ብለዋል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊው ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ኤፍኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እንዲሁም በቀጣናው ትክክለኛ እና ፍትሐዊ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናዋን ለመጎናፀፍ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ አቅደው የሚሰሩ  ጠላቶች አሁንም አሉ ሲሉ ዶ/ር ቢቂላ ተናግረዋል።

በትጥቅ ትግል እና በሌሎች መንገዶች ያልተሳካላቸውን ተልዕኮ በሐሰተኛ መረጃ እና በጥላቻ ንግግር በኩል የህዝቦችን መተማመን በመሸርሸር ወደ ግጭት ለማስገባት የሚደረግ ሙከራ በመሆኑ እንደ ሉዓላዊነት ጥቃት ይወሰዳል ብለዋል።

ዜጎችም ጉዳዩን ከኢትዮጵያ ክብር እና ሉዓላዊነት አንፃር በማየት ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግርን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ዶ/ር ቢቂላ ጥሪ አቅርበዋል::

Image
ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር የሉዓላዊነት ጥቃት አካል ነው - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)