የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ 2018 በጀት አመት 1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም ገመገመ።
(ሀላባ፣ ጥቅምት 8/ 2018 )
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ከተጠሪ ተቋማት ፣ ከዞን ፍትህ መምሪያ እና ከልዩ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ጋር የበጀት አመቱን 1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ገምግሟል።
በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን፣ የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ ወንጀልን በመከላከል፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በማከልም በፍትህ ተቋማት አሰራርን ከማዘመን አንፃር የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊው የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ የህዝብ እርካታን ከፍ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
ስብዕና ያለው የፍትህ ሰራዊት በመገንባት ፍትሃዊና ያልተንዛዛ የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲረጋገጥ በቅንጅት መሥራት እደሚገባም አመላክተዋል።
በመቀጠልም የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም ሪፖርት በቢሮው ልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ፍቅሩ ከቀረበ በኋላ ሠፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም በድክመት እና በጥንካሬ በተነሱት ጉዳዮች ላይ አስተያየት ከተሰጠ በኋላ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
(ለዘገባው የፍትህ ቢሮ መ/ኮሙኒኬሽን)