Skip to main content

"ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የጸረ ፆታዊ ጥቃት የነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ
***
ታህሳስ 8/2018 
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ''
''ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለሀገር ግንባታ'' በሚል መርህ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ግዜ በሀገራችንና በክልላችን ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የነጭ ሪቫን ቀን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተከበረ።

በመክፈቻ ንግግር መድረኩን ያስጀመሩት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኢያሱ ሻንቆ በበኩላቸው የሴቶች ጥቃት በአለም አቀፍ በተለያዩ መልኩ የሚፈጸምና በሰዎች አካል ፣ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት የሚደርስ ድርጊት መሆኑን ገልፀዋል።

ምክትል ሃላፊ አቶ ኢያሱ ሻንቆ አያይዘውም አካላዊ ፣ስሜታዊ ፣ ሥነልቦናዊ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጉዳት የመብት ጥሰት በማድረስ የሚፈጸም እኩይ ድርጊት መሆኑን ጠቁመ፣

የነጭ ሪቫን ቀን በወንዶች በሴቶች ህጻናት ላይ ማንኛውም ጥቃት ላለመፈጸም እንድሁም ጥቃቱ በሌሎች ስፈጻም ዝም አለማለትም ጭምር መሆኑን ገልፀዋል።

ለመድረኩ የተዘጋጀውን ሰነድ በወ/ሮ አብዮት ሜኔዶ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በሌለ በኩል ፀረ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት በሴቶችና ህፃናት ላይ እንዳይደርስ ቃል የማስገባት ስነስርዓት እንድሁም የኬክ ቆረሳ ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኢያሱ ሻንቆ ፣የሴ/ህ/ጉ/በልማት መካተት ተጠቃሚነት መረጋገጥ ዘርፍ ወ/ሮ አብዮት ሜኔዶ በጋራ መርተውታል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኢያሱ ሻንቆ እንደተናገሩት ፆታዊ ጥቃቶች በዋነኛነት በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ስነ ልቦናዊ እና አካላዊ ጫና መሆኑን ጠቁመው በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደረሱ ጥቃቶች በጋራ የመከላከል የሁሉም ድርሻ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

ወ/ሮ አብዮት ሜኔዶ በበኩላቸው በሴቶችና ህፃናት መብትን ለማስከበር ፣ የሴቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤን እንዲፈጠር በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኢያሱ ሻንቆ፣የፍትህ ቢሮ ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
ዘገባው ፦ የቢሮው መንግስት ኮሚኒኬሽን

Image
ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለሀገር ግንባታ" በሚል መሪ ቃል የጸረ ፆታዊ ጥቃት የነጭ ሪቫን ቀን ተከበረ