የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ '' ከአኩሪ ታሪከ ፣ ወደ ብሩ አድማስ'' በሚል መሪቃል 130ኛ ውን የአድዋ ድል በዓል በድምቀት አከበረ።
ሀላባ ቁሊቶ የካቲት 24 /2018 ዓ/ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ 130ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በድምቀት ባከበረበት ወቅት ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር በማድረግ መድረኩን ያስጀመሩት የፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰላሙ ዳንኤል ሲሆኑ በንግግራቸውም የአድዋ ድል ለኢትዮጵያውያን የታሪክ ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን ዳግም እንዳይ ደፍሩን አድርገን ለወራሪዎችና ለጨቋኞች የማይበገረው ኢትዮጵያዊ ክንዳችንን ያሳየንበት ፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት የሆንበት ወደር የለሽ ፅናት ለዓለም ያበሰርንበትና ለብሄራዊ ክብራችን ያለንን ቁርጠኝነት ያስመሰ ከርንበት ዘመን ተሻጋሪ እሴታችን ነው ብለዋል፡፡ በመቀጠልም ድሉ ከትላንቱ የአድዋ ጦርነት ባሻገር ለዛሬው ሀገራዊ ግንባታና ለነገው የብሄራዊ ከፍታ እንደ መነሻ ሊያገለግለንና ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል።
በመቀጠልም ኢትዮጲያ በታሪኳ ታላቅ ስልጣኔ የነበራት እና የነጻነት ተምሳሌት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው አሁን ያለንበት ወቅት በዓድዋ መንፈስ ፈተናዎችን አሸንፈን ያንን ታላቅነት ዳግም የምናረጋግጥበት ዘመን ሊሆን ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም ከእርስ በርዕስ ግጭትና ጥላቻ ወጥተን ሀገርን የሚያሻግር አዲስ አስተሳሰብ በማምጣት በየተሰማራንበት የሥራ ዘርፍ ሀገሬ ከእኔ ምን? ትጠብቃለች ብሎ የሚጠይቅ ትውልድ ማፍራት ስንችል በመሆኑ ልዩነታችንን የጥፋት ሳይሆን የውበት ምንጭ ማድረግ ከቻልን ሀገራችን ታፍራና ተከብራ፤ ዜጎቿ በልፅገውና ሰላም አግኝተው የምናይበት እሩቅ አይሆንም :: ይህ እንዲሆን ካለፈዉ ታሪካችን ጥንካሬን በመውስድ ዛሬ ላይ በርትተን በመሥራት የተሻለ ነገን ለትውልድ ማስረከብ እና ለዚህ የጋራ ግባችን በጋራ መቆም የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ገልፀዋል።
በመቀጠልም የዓድዋ 130 ኛ መታሠቢያ በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው የመወያያ ሠነድ በአቶ አሸብር አዲሱ ቀርቦ በተሣታፊዎች ሠፊ ውይይት ተደርጎበታል። በመጨረሻም በፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና በህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ በአቶ አብርሃም በድሩ እና በፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ እና ኮርፖሬት ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ሠላሙ ዳንኤል የማጠቃለያ ሀሳብ ተሰጥቶበት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
ዘገባው:- የቢሮው መ/ኮ