Seble
Mon, 04/20/2026 - 10:43
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገመገመ።
ሀላባ፣ ሚያዚያ 8/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከአመራሮችና ከማናጅመንት አካላት ጋር በመሆን በጥልቀት ገምግሟል።
በዚሁ የግምገማ መድረክ የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን የተገኙ ሲሆን፣ የ9 ወራት አፈፃፀም ሪፖርቱ በልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ፍቅሩ በተደራጀ ሁኔታ ቀርቧል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ አመራሮችና ማናጅመንት አባላት ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ጠንካራ አፈፃፀሞችን እና የሚሻሻሉ ዘርፎችን ለይተው ገንቢ አስተያየት አቀርበዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በግልፅ በማብራራት፣ በተለይም የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከር እና የታዩ ድክመቶችን በተግባር ማሻሻል ላይ እንዲተኮር አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን
Image