ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ኢ-መደበኛ ፍልሰትና በሰው መነገድ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማዕቀፍ ማጠናከርን ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሄደ
ሀላባ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ኢ-መደበኛ ፍልሰትን፣ በሰው መነገድን እና ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ደንብ ቁጥር 32/2017 አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ ም/ኃላፊ እና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ ሲሆኑ በንግግራቸው እንደገለጹት :- በሰው መነገድና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀሎች በዜጎች ህይወት፣ ደህንነትና ሰብዓዊ መብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ እና ችግሩን በህግ፣ በቅንጅትና በህዝብ ተሳትፎ ለመከላከል የተጠናከረ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ኃላፊው በማከልም አዋጁና ደንቡ የሰው መነገድን፣ ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን እና ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገርን ለመከላከል እንዲሁም የፍልሰት አስተዳደርን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆናቸው ተጠቁሟል። በተለይም የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የህዝብ አደረጃጀቶች፣ የሀይማኖት ተቋማት እና የሙያ ማህበራት በቅንጅት እንዲሰሩ የሚያግዝ የትብብር ሥርዓት መዘርጋቱንም ገልጸዋል።
በክልሉ በተለይም በሀድያ፣ በከምባታ ጠምባሮ፣ በጉራጌ፣ በምዕራብ ጉራጌ፣ በስልጤ እና በሀላባ ዞኖች የሚስተዋሉ በሰው መነገድና ህገ-ወጥ ፍልሰት ችግሮችን ለመቀነስ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ፣ የክትትልና የቅንጅት ሥራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንም ጠቅሰዋል።
በመቀጠልም ለውይይት የተዘጋጀውን ሠነድ በጥሩ ሁኔታ በማቅረብ ስልጠናውን የሰጡት የቢሮው ዐቃቤ ህግ አቶ ጢሞትዮስ ዋርጎ እና የቢሮው የፍልት ጥብብር ጥምረት አስተባባሪ አቶ ታደሰ ወንድሙ ሲሆኑ
በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮች፣ ፈፃሚዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ችግሩን ለመከላከል የራሳቸውን ድርሻ በተጠናከረ መልኩ ለመወጣት ቁርጠኝነታቸውን የገለፁ ሲሆን፣ ህብረተሰቡም ከህገ-ወጥ የፍልሰት መንገዶች እንዲርቅ እና ህጋዊ አሰራሮችን እንዲከተል ጥሪ ቀርቧል።
ፍቅርተ ዘለቀ
የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን