የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምና የ100 ቀናት ዕቅድ ገምግሟል
ሀላባ፦ ጥቅምት 12/2019 ዓ/ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ከቢሮው ሠራተኞች ጋር ገምግሟል። በዚሁ መድረክ የ100 ቀናት ዕቅድም በመገምገም፣ የታዩ ጥንካሬዎችን ለማጠናከር፣ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታትና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለመለየት ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ በአቶ ጌታሁን ፍቅሩ ቀርቧል። ሪፖርቱ ከቀረበ በኋላም ተሳታፊዎች በዕቅዱ አፈጻጸም፣ በተከናወኑ ተግባራትና በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሰፊና ገንቢ ውይይት አካሂደዋል።
ውይይቱን የፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የወንጀልና ፍትሐብሔር ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ሻንቆ እንዲሁም የተጠሪ ተቋም የግብር ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ በቱላ አብደላ በጋራ መርተዋል።
በውይይቱ ሠራተኞች በሥራ አፈጻጸሙ ሂደት የታዩ ችግሮችን፣ መሻሻል ያለባቸውንያ ጉዳዮችና ለተሻለ ውጤት መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በጥልቀት አንስተዋል። በተጨማሪም የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም፣ ያሉ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠልና ለማጠናከር፣ የታዩ ድክመቶችን ለማረም እንዲሁም በቀጣይ የሥራ አፈጻጸም ላይ መሻሻል ለማምጣት የሚያስችሉ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሥራ አቅጣጫዎችን በማብራራት፣ የታዩ ጥንካሬዎችን በማጠናከርና ድክመቶችን በማረም የተሻለ፣ ውጤታማና ተደራሽ የፍትህ አገልግሎት ለሕዝብ ለማቅረብ በቅንጅት፣ በትጋትና በተጠያቂነት መሥራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ፍቅርተ ዘለቀ
የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን