የሰብዓዊ መብቶች ድርጊት መርሀ ግብር ማስተባበሪያ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
የማስተባበሪያወ ዋናዋናተግባርናኃላፊነት
- በክልል ደረጃ የድርጊት መርሀ ግብሩን አፈጻጸም በክልላዊ አስተባባሪ ኮሚቴው በሚሰጡት አቅጣጫዎች መሰረት ይከታተላል።
- በመርሀ ግብሩ እንዲከናወኑ የተቀመጡ ተግባራት፤ ፈጻሚ አካላት ተብለው በተለዩት የክልል ተቋማት ዕቅዶች ውስጥ መካተታቸውን ይከታተላል፤
- በየተቋማቱ ውስጥ ከተደራጁት የድርጊት መርሀ ግብሩ ተወካዮች/Focal Person/ ጋር በቅርበት ይሰራል፤
- ተቋማት በየሩብ ዓመቱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቶችን በወቅቱ አሰባስበው መላካቸውን ይከታተላል፤
- በየሩብ ዓመቱ ክልል አቀፍ የድርጊት መርሀ ግብሩን አፈጻጸም ሪፖርት በማጠናቀር ለክልላዊ አስተባበሪ ኮሚቴ እና ለፌዴራል ፍትህ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ድርጊት መርሀግብር ፅ/ቤት ያቀርባል፤
- የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ የሚቀርቡ አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን መመርመር፣ እንዲመረመሩ ማድረግ፤
- ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በፌደራል ደረጃ የወጣው የብሔራዊ ሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሀ-ግብር በክልሉ ውስጥ ያለውን ተፈፃሚነት መከታተል፤ በክልል-አቀፍ ደረጃ ተሳታፊ የሚሆኑትን ወገኖች እንቅስቃሴ ማስተባበር፤ ለሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ማቅረብ፤
- ሀገሪቱ ያፀደቀቻቸው ወይም የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍና አህጉራዊ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች በክልሉ ውስጥ ያላቸውን ተፈጻሚነት መከታተል፤ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ ሲቀርብለት ብሔራዊ የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት ረገድ መተባበር፣ ማገዝ፤
- የህግ አስከባሪ አካላት የሃይል አጠቃቀምና ተጠያቂነት ሥርዓት በተመለከተና ሌሎች ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የተያያዙ የህግ ማዕቀፎች እንዲዘጋጅ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች አስመልክቶ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተባብሮ መስራት፤
- ሌሎች በዘርፉ ተለይተው የሚሰጡትን ተግባራት ማከናወን፤