#የሳምንቱ #አበይት #ዜናዎቻችን....
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ብሄራዊ ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀመሩ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ለተማሪዎቹ መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
.......................................//.........................................
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እና በምግብ እራስን ለመቻል የተጀመረው ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስጀመረ
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 5፣ 2017 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ አስጀምሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የጽ/ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አለምጸሀይ ጳውሎስን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
በማስጀመሪያው የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ እና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
በተጨማሪም በአበሽጌ ወረዳ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ፣ የአቅመ ደካሞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና የጽዱ ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቭ አካል የሆነው የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ተጀምሯል፡፡
የሥራ ኃላፊዎቹ በዞኑ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል ሲል ኤፍ ኤም ሲ ዘግቧል።
በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በክልሉ ተግባራትን በቅንጅት፣ በእዉቀትና በክህሎት የመፈጸምና የማስፈፀም ልምምድ እየተሻሻለ መጥቷል፤ የተናጠልና የቡድን ሀላፊነትን የመወጣት ዝግጁነትና ጥረትም እየጎለበተ ይገኛል።
በተጠናቀቀዉ በጀት ዓመት በክልሉ ተግባራትን በቅንጅት፣ በእዉቀትና በክህሎት የመፈጸምና የማስፈፀም ልምምድ እየተሻሻለ መጥቷል፤ የተናጠልና የቡድን ሀላፊነትን የመወጣት ዝግጁነትና ጥረትም እየጎለበተ ይገኛል።
እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ፣
ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች የክረምት ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች የክረምት ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በይፋ ተጀመረ
(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 4/2017)፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከመላው ኢትዮጵያ ለተወጣጡ የክረምት ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች በሆሳዕና ከተማ አቀባበል ተደርጓል።
"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው ሀገር አቀፍ የወሰን ተሻጋሪ የክረምት ወራት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች አገልግሎት በክልሉ መካሄድ ጀምሯል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ሌሊሾ ወጣቶቹን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉት ወቅት፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዓለማ፤ ወጣቶችንና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎችን በስፋት እንዲሳተፉ በማድረግ የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍታትና የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ባህል ሆኖ እንዲጎለብት የማድረግ ሚናን መጨወት መሆኑን ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ3ኛ ቀን ውሎው በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ እየመከረ ነው::
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ3ኛ ቀን ውሎው በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ እየመከረ ነው::
(ሆሳዕና፣ሐምሌ 4/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ እየመከረ ነው
መስተዳድር ምክር ቤቱ በ3ኛ ቀን ውሎው በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ የክልሉ መ/ኮ
ባሳለፍነው አመት የክልሉን ጸጥታ በማስከበር የህዝቡ ሰላም እንዲጠበቅና የክልሉ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ የተሰሩ ፖሊሳዊ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
ባሳለፍነው አመት የክልሉን ጸጥታ በማስከበር የህዝቡ ሰላም እንዲጠበቅና የክልሉ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ የተሰሩ ፖሊሳዊ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
በቀጣዩ አመት በክልሉ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የብሄር ብሄረሰቦች በኣልና ሀገራዊ ምርጫ ከወዲሁ የተሟላ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል ።
በተጠናቀቀው በጀት አመት የክልሉን ጸጥታ በማስከበር የህዝቡ ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅና የክልሉ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዳይስተጓጎሉ ለማድረግ የተሰሩ ቅንጅታዊ የፖሊስ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
ኮሚሽኑ የ2017 በጀት አመት አፈጻጸሙን የዞንና ልዩ ወረዳ የፖሊስ አመራሮች በተገኙበት በሆሳዕና የገመገመ ሲሆን በዚሁ ወቅት እንዳለው ግጭቶችን አስቀድሞ በመከላከል የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝና ዘላቂ እንዲሆን ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ።
(ሃምሌ 3/2017)፣ በተሻሻለው አዲሱ አማራጭ የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ መመሪያ ላይ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች በዱራሜ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህፃናት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አምሪያ ሲራጅ ስልጠናውን በንግግር በከፈቱበት ወቅት ቢሮው የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተፈጥሮአዊ እና ሰውሰራሽ አደጋዎች ለተጋለጡ ህጻናት በማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ የተለያዩ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን ኃላፊዋ ተናግረዋል።
ወይዘሮ አምሪያ ባልተደራጀ መንገድ ሲሰጥ የነበረውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የተደራጀና ዘላቂ መፍትሄ በሚያመጣ መልኩ መፈጸም ማስቻል የስልጠናው አላማ መሆኑን ተናግረዋል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን መንግስት የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ እየመከረ ነው
መስተዳድር ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው የክልሉን መንግስት የ2017 ዓ.ም አፈጻጸም አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ እየመከረ ነው
ሆሳዕና፣ ሐምሌ 3/2017 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ም/ቤት በሁለተኛ ቀን ውሎው በክልሉ መንግስት የ 2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርት ላይ እየመከረ ነው።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በ29ኛ መደበኛ ስብሰባው በቀረቡለት ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ውሳኔ ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ብሄራዊ ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀመሩ ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ብሄራዊ ፈተና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀመሩ ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ለተማሪዎቹ መልካም ውጤት ተመኝተዋል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ(ዶ/ር)፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ እና ሌሎችም ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች ተገኝተዋል።