Skip to main content
የዐቃቢያነ ህግ አስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
  •         የዓቃብያነ ሕግ ቅጥር፣ ዝውውር፣ ምደባና ደረጃ እድገት ስራዎችን ይሰራል፤ የውሳኔ ሀሳብ ለቃቤ ሕግ አስተዳደ ዋና ጉባኤ በማቅረብ ያፀድቃል፤

  •        የዐቃብያነ ህግ የዲስፕሊን ጉዳዮችን በማጣራት የውሳኔ ሀሳብ ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዐቃብያነ ህግ አስተዳር ዋና ጉባኤ ውሳኔ እንዲሰጥበት ያደርጋል፤ ውሳኔው ይፈጽማል፤

  •        የዐቃብያነ ህግ ደመወዝ፣ ጥቅማ ጥቅም እና የመሳሰሉ ጉዳዩችን ያካተተ ረቂቅ ንብ አዘጋጅቶ ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዋና ጉባኤ ተተችቶ ለመስተዳድር ም/ቤት እንዲቀርብ ያደርጋል፤

  •        በዋናው ጉበኤ የሚሰጡትን የተለያዩ ስራዎች ጨምሮ የዓቃብያነ ህጉን መረጃ በአግባቡ የመያዝ እና አስተዳደራዊ አገልግልቶችን ይሰጣል፡፡

  •        ዐቃበያነ ህግ አስተዳደር ዋና ጉባኤ የሚወስናቸውን እና የሚሰጣቸውን ውሳኔዎች እና ትዕዛዞች አፈጻፀም መከታተልና ሲፈለግ ለጉባኤው ያቃርባል፣

  •        በዐቃብያነ ህግ የሚቀርቡ የዲስፕሊን ጉዳዮችን በማደራጀት ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ የሚፈቱበትን ሁኔታዎች ማማከር፣ 

  •        የዐቃቢያነ ህግ መብት ጥያቄዎችን በመቀበል ለቢሮ ኃላፊ በማቅረብ በዋናው ጉባኤ የሚወሰንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣ 

  •        የክልሉን ዐቃብያነ ህግ ማስተዳደር ጋር ተያይዞ በቢሮ ኃላፊ የሚሰጡ ማንኛውንም ህጋዊ ትዕዛዝ መፈጸምና ማማከር፡፡