Skip to main content

በ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ላይ አስተያየት ይስጡ!

በ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ላይ አስተያየት ይስጡ!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት እያዘጋጃቸው ከሚገኙ ረቂቅ መመሪያዎች መካከል አንዱ የ«የይቅርታ ተጠቃሚ የሕግ ታራሚዎች ምልመላና መረጣ ረቂቅ መመሪያ» ነው።

ቢሮው ረቂቅ መመሪያውን ይበልጥ የተሟላና ጥራት ያለው ለማድረግ በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች ከሚሰበሰቡ ግብዓቶች በተጨማሪ፣ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ ገንቢ ሐሳቦችንና አስተያየቶችን በቢሮው ድረ ገጽ ፣ በቴሌግራም ገጽ እና በነፃ የጥሪ ማዕከል በ 8651 አማካኝነት ለመቀበል ይፈልጋል።
ስለሆነም በረቂቅ መመሪያው ላይ ያላችሁን ገንቢ ሐሳብና አስተያየት በተዘጋጁት መገናኛ አማራጮች እንድታደርሱን በአክብሮት እንጋብዛለን።

"የእርስዎ ገንቢ ሐሳብ የተሻለ የሕግ ሥርዓት ግንባታ አካል ነው!"
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ

የዐቃቤ ህግ አስተዳደርን እና ሙያዊ አፈጻጸምን ለማጠናከር የተዘጋጁ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በማኔጅመንት ውይይት ግብዓት ተሰበሰበ

የዐቃቤ ህግ አስተዳደርን እና ሙያዊ አፈጻጸምን ለማጠናከር የተዘጋጁ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በማኔጅመንት ውይይት ግብዓት ተሰበሰበ******

ሀላባ፣ ሰኔ 24/2018 ዓ.ም. የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቤ ህግ ተቋማዊ አስተዳደርን፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርንና የሥራ አፈጻጸምን የበለጠ ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ውጤታማ ለማድረግ ያለሙ አራት ረቂቅ መመሪያዎችን ለማፅደቅ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ ከቢሮው ኃላፊዎችና ከማኔጅመንት አባላት ጋር ለሁለት ቀናት የቆየ ዝርዝር ውይይት አካሂዷል።

በሰኔ 23 እና 24/2018 ዓ.ም. በሀላባ በተካሄደው የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ፣ የዐቃቤ ህግ ሥነ-ምግባር አፈጻጸም፣ የቅጥር፣ የምደባና የዝውውር አፈጻጸም፣ የዐቃቤ ህግ አስተዳደር ጉባኤ አባላት የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም የዐቃቤ ህግ የሥራ አፈጻጸም ምዘናን የሚመለከቱ አራት ረቂቅ መመሪያዎች በዝርዝር ቀርበው ተመርምረዋል።

በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመግታት የህግ ማዕቀፍ ማጠናከር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ

በሰው መነገድና ሰውን በህገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመግታት የህግ ማዕቀፍ ማጠናከር ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ
ሀላባ፣ ሰኔ 11/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ HOPE FOR JUSTICE ከተባለ ግብረ ሠናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ኢ-መደበኛ ፍልሰትን፣ በሰው መነገድን እና ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ደንብ ቁጥር 32/2017 አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል።
በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የHOPE FOR JUSTICE የፕሮግራሞች ዳይሬክተር አቶ ፈይሳ ተፈራ ሲሆኑ፣ የመክፈቻ ንግግሩን ያቀረቡት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ ናቸው።

የሥራ ሥነ-ምግባር ግንባታ ለተቋማት ውጤታማነትና ለተገልጋይ እርካታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

የሥራ ሥነ-ምግባር ግንባታ ለተቋማት ውጤታማነትና ለተገልጋይ እርካታ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
ሀላባ፣ ሰኔ 2/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ለቢሮው አመራሮችና ሠራተኞች በሥራ ሥነ-ምግባር ዙሪያ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ።
በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም በድሩ፣ የሥራ ሥነ-ምግባር በታታሪነት፣ በተጠያቂነትና በቁርጠኝነት ሥራን በመከወን የሚረዳ መሠረታዊ እሴት መሆኑን ገልፀው፣ ተቋማት ተልዕኳቸውን በተሳካ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችላቸው ዋና መሠረት መሆኑን አስረድተዋል።

የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 እና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ የዐቃቢያነ ህግ አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተካሄደ

የቅጣት አወሳሰን መመሪያ 3/2017 እና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዙሪያ የዐቃቢያነ ህግ አቅም ማጎልበቻ ሥልጠና ተካሄደ 

ሀላባ፣ ግንቦት 15/ 2018 ዓ.ም 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 3/2017 እና በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ዘርፍ የዐቃቢያነ ህግ ሚናን ለማጠናከር ያለመ ሥልጠና ለክልሉ፣ ለዞን እና ለልዩ ወረዳ ዐቃቢያነ ህጎች በሆሳዕና ከተማ ለሁለት  ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረዉ ስልጠና ተጠናቀቀ ። 

ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ኢ-መደበኛ ፍልሰትና በሰው መነገድ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማዕቀፍ ማጠናከርን ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘውን ኢ-መደበኛ ፍልሰትና በሰው መነገድ ወንጀል ለመከላከል የህግ ማዕቀፍ ማጠናከርን ያማከለ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ሀላባ ግንቦት 4/2018 ዓ.ም 

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ ኢ-መደበኛ ፍልሰትን፣ በሰው መነገድን እና ህገ-ወጥ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና ደንብ ቁጥር 32/2017 አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክርና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በዱራሜ ከተማ ተካሂዷል።

በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ።

በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን መከላከል እና ምላሽ አሰጣጥ ዙርያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ።
*****
ሚያዝያ  20 / 2018 ዓ.ም ሀላባ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል እና ድርጊቱ ሲፈፀም ፈጣንና ፍትሃዊ ምላሽ ለመስጠት ያለመ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በወራቤ ከተማ ተሰጠ።

በሥልጠናው  በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች በተለይ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ-እድሜ ጋብቻን ለመከላከል እና ተፈጽሞ ሲገኝ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የሚሰሩ ዐቃቤያነ-ህጎች፣ መርማሪ ፖሊሶች እና የማህበራዊ ሳይንስ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገመገመ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፍትህ ቢሮ የ9 ወር ዕቅድ አፈፃፀም በጥልቀት ገመገመ።
ሀላባ፣ ሚያዚያ 8/2018 ዓ.ም
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ከአመራሮችና ከማናጅመንት አካላት ጋር በመሆን በጥልቀት ገምግሟል።
በዚሁ የግምገማ መድረክ የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን የተገኙ ሲሆን፣ የ9 ወራት አፈፃፀም ሪፖርቱ በልማት ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ፍቅሩ በተደራጀ ሁኔታ ቀርቧል።
በቀረበው ሪፖርት ላይ አመራሮችና ማናጅመንት አባላት ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ጠንካራ አፈፃፀሞችን እና የሚሻሻሉ ዘርፎችን ለይተው ገንቢ አስተያየት አቀርበዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ አቶ አክመል አህመዲን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በግልፅ በማብራራት፣ በተለይም የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከር እና የታዩ ድክመቶችን በተግባር ማሻሻል ላይ እንዲተኮር አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የቢሮው መ/ኮሚኒኬሽን 

የ 2018 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ።

የ 2018 ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ
ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። 

መጋቢት:-15 /2018 ዓ.ም 

የክልሉ ፍትህ ቢሮ በምርጫ ህግ ፤ በጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመከላከል ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ በቡታጀራ ከተማ  አካሂዷል። 

በመርሀ ግብሩም ከዞንና ከልዩ ወረዳ ፍርድ ቤቶች የተውጣጡ ዳኞች፣ ከፍትሕ መምሪያዎች የተወከሉ ዓቃቢያነ ሕግ፣ ከፖሊስ መምሪያዎች የተገኙ መርማሪ ፖሊሶች እና የሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ -ህግ የሙያ ሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ለማሻሻል ከቢሮው ዐቃቢያነ ህጎች ጋር ውይይት አደረገ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የዐቃቢያነ -ህግ የሙያ ሥነ-ምግባር ረቂቅ መመሪያ ለማሻሻል ከቢሮው ዐቃቢያነ ህጎች ጋር ውይይት አደረገ።

ሀላባ መጋቢት 1/2018 ዓ.ም

ቢሮው የ0ቃ ቢያነ - ህግ የሙያ ሥነ - ምግባር ረቂቅ መመሪያን በማዘጋጀት ከቢሮው ዐቃቤ ህጎች ጋር በመወያየት ረቂቁን በተሻለ ለማጎልበት አጋዥ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለማግኘት በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ከተወያይዎች ጠቃሚና ገንቢ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል። ረቂቁን ባዘጋጁት ቡድኖችም ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ረቂቁን በቀጣይ ለማሻሻል ወሳኝ ግብዓቶች ማግኘታቸውን ገልፀዋል።

ለዘገባው የቢሮው መ/ኮ