Skip to main content

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ግንባታ

ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ግንባታ 
የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነስ  የአምራቹንና ሸማቹን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተግባር መሆኑን  የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ

(ሆሳዕና ፣ሰኔ 27/2017) ቢሮው  በዱራሜ ከተማ ለሚገነባው  ከሰንበት እስከ ሰንበት ዘመናዊ የግብይት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የማኖር መርሐ ግብር አካሂዷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ እንደገለፁት  
የሰንበት ገበያ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በህገወጥ ነጋዴዎች ሳይበዘበዙ  ኑሮ ውድነትን ለማቃለል ሳምንቱን በሙሉ የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።

የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ብሎም አርሶ አደሩን ከሸማቹ ጋር  በቀጥታ በማገናኘት  የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ተግባር እንደሆነም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ተጀመረ

ሆሳዕና ፣ ጥር 2፣ 2017 የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ለኢኮኖሚና ፋይናንስ ምህዳራችን ታሪካዊ በሆነ እጥፋት የኢትዮጵያን የመጀመሪያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ደወል ደውልናል ብለዋል።
ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ባላት፣ ለብልጽግና ሰፊ እምቅ አቅምና ምቹ መንገድ እየተነጠፈላት ባለችው ኢትዮጵያ ባለሃብቶች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡