Skip to main content

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነዉ፣

ርዕሰ መስተዳድር  እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም  ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነዉ፣
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 9፣ 2017፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛል።

ጥናቶቹ ከተሞችንና ከተሜነትን በዘመነ መንገድ በመምራት ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር  እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስለመሆናቸዉ ተገልጿል ።

የጥነት ሠነዶቹ በከተምች ፈርጅ ሽግግሮችን ፣ በከተማ ተቋማዊ አደረጃጃትና አሠራሮች ማሻሻያዎችን እና  ፣በከተሞች ከመሬት ጋር የተያያዙ ህገዎጥነቶችን በመከላከል  ዙሪያ ያተኮሩ ሲሆን የጥናት ሠነዶቹ ቀርበዉ ዉይይት እየተካሄደ  ይገኛል።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

በዱራሜ ከተማ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ የቦታ ርክክብ ተደረገ።

በዱራሜ ከተማ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ የቦታ ርክክብ ተደረገ።

በተለያዩ ምክንያቶች ኮንትራቱ ተቋርጦ የነበረው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል  በአዲስ መልክ  ጨረታ በማውጣት ለአሸናፊው  ተቋራጭ የሳይት ርክብክብ መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል ። ግንባታው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑም ተመልክቷል።

የቢሮው ምክትልና  የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሠርካለም ሣሙኤል ተቋርጦ የነበረው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በየደረጃው ከሚመመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ርብርብ ፕሮጀክቱ በድጋሚ እንዲቀጥል ማድረግ ተችሏል ነው ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 9/2017)፣ መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ ተካሂዷል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት፥ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በመከላከያ በኩል 18 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሠራዊት ተተክለው፣ ለምግብነት የደረሱ የብርቱካን፣ ሎሚ፣ ሮማን፣ ፓፓዬና ሌሎችም ፍራፍሬዎች ለአባላቱ እየቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ  አቶ ጌትነት ታደሰ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 9/2017)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ  አቶ ጌትነት ታደሰ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች በሆሳዕና ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የክልል ተቋማትን ተመልክተዋል።

በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ የሚደረግበት እና በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ  እየተገነቡ የሚገኙ የክልል ተቋማት  የቢሮ ህንጻ ግንባታ በተያዘው በጀት አመት እየተፋጠነ ይገኛል።

በሰባት የክልል ማዕከል ከተሞች ለሚገነቡ ቢሮዎች መጋቢት 1/2017 የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል።

በተስፋዬ መኮንን

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እያከናወነ ያለው ስራዎች አበረታች መሆኑን የክልሉ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እያከናወነ ያለው ስራዎች አበረታች መሆኑን የክልሉ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ገለጸ
=====

ሀምሌ 9/2017) የምክር ቤቱ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።

በተመሳሳይ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና ሴቶችና ህፃናት ቢሮ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በቋሚ ኮሚቴዎች ተገምግሟል።

የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እንደገለፁት ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተግባራትን ለመፈጸም የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል።

የፍርድ ቤቶችን ውጤታማነትና ቅልጥፍና በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እና መዘገብ የመጠራት ስራ በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተ

ሆሳዕና፣ሐምሌ 7/2017)በሞባይል ባንኪንግ ማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ላይ የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደመሰረተ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተገልጿል።

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2016/2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ከተለያዩ የዘርፉ ተጠሪዎች ጋር እየገመገመ ባለበት መድረክ ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ተወካይ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ ባቀረቡት ሪፖርት፣ በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት ከ116 ግለሰቦች ላይ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በሞባይል ባንኪግ በማጭበርበር ወንጀል በተጠረጠሩ 20 ግለሰቦች ላይ የፌደራል ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደተመሰረተባቸውገልጸዋል።

አመራር አካዳሚው በጥናትና ምርምር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራቱን የክልሉ ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

አመራር አካዳሚው በጥናትና ምርምር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራቱን የክልሉ  ምክር ቤት ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

(ሆሳዕና፦ሀምሌ 8/2017) ቋሚ ኮሚቴው የክልሉ አመራር አካዳሚ  2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ገምግሟል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ  አቶ ግዛቸው ዋሌራ እንዳሉት በአካዳሚው በጥናትና ምርምር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራቱን ገልፀዋል።

አካዳሚው ለተለያዩ አስፈጻሚዎችና ፈጻሚዎች የአቅም ግንባታ እየሰጠ ያለበት አግባብ የሚያበረታታ ነው ብለው  በጥናትና ምርምር ዘርፍ በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆንም ጥናቱ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሊሆኑ ይገባል ነው ያሉት።

አካዳሚው እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ክፍተቶችን በመለየት እየሰጠ ያለው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች  ተጨባጭ ለወጥ አምጥቶ የህዝብ ተጠቃሚነት እስከሚረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ላቦራቶሪን በማደራጀት በማስመረቅ የምርመራ አገልግሎቶችን በማስጀመርና በማጠናከር ረገድም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተመላከተ።

በክልሉ ላቦራቶሪን በማደራጀት በማስመረቅ የምርመራ አገልግሎቶችን በማስጀመርና በማጠናከር ረገድም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተመላከተ።

ሆሳዕና ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 ዓ.ም ዓመታዊ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት አመት የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት እንድ ክልል አምስት ግቦችን በማስቀመጥ ወደ ስራ መገመቱን ጠቅሰው ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፍን ማፍጠን በሚያስችል መልኩ በርካታ ስራ መሰራቱን ገልጸዋል።

ከጤና ተቋማት ተደራሽነት አገልግሎት አቅርቦት ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ለህብረተሰቡ ከማድረስ፣የህብረተሰብን የጤና ሁኔታን ማሻሻል ጥራት ፍትሀዊነት ተደራሽነትን ታሳቢ ያደረገ፣ህብረተሰቡን ከድንገተኛ አደጋዎች የመጠበቅ ስራዎችን ቢሮው በትኩረት መስራቱን ኃላፊው አስታውቀዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ እና የግብርና ግብአቶችን በአግባቡ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለፀ።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ እና የግብርና ግብአቶችን በአግባቡ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉ ተገለፀ።

(ሆሳዕና፦ሀምሌ 7/2017)፣ የክልሉ ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግብርናን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ  ወ/ሮ ልክነሽ ስርገማ እንዳሉት የአርሶአደሩን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ በግብርና ቢሮ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ነው ብለዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂ እና የግብርና ግብአቶችን በአግባቡ በመጠቀም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉን በግምገማው አንስተው ገበያ ተኮር የአመራረት ዘዴን በመከተል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገው ርብርብ ተጫባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል።

ሙስናን በቅንጅት በመከላከል የህግ የበላይነት እንዲሰፍን በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ

ሙስናን በቅንጅት በመከላከል የህግ የበላይነት እንዲሰፍን በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች  ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ

(ሆሳዕና፦ ሀምሌ 8/2017) ቋሚ ኮሚቴው  የክልሉን ስነ-ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ገምግሟል።

የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ   ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እንዳሉት ሙስናን በቅንጅት በመከላከል  የህግ የበላይነት  እንዲሰፍን አበክሮ ሊሰራ ይገባል።

በፀረ ሙስነ ትግል ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የተካሄደበት አግባብ ጥሩ ሆኖ ሙስናን በመከላከልና ሙስናን የሚጸየፍ ዜጋን ለማፍራት ሌተ ቀን መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።