በክልሉ ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል - አቶ ኡስማን ሱሩር
በክልሉ ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል - አቶ ኡስማን ሱሩር
(ሆሳዕና፣ሰኔ 30/2017)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ነገ ሀምሌ 1/2017 ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ እና የገጠር ኮሪደር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እንደሚካሔድም ተመላክቷል
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለመገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ነገ ሀምሌ1/2017 ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ እና የገጠር ኮሪደር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ይካሄዳል ብለዋል።
በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በሚካሄደው ክልላዊ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ከ500 ሚሊየን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉም ኃላፊው በመግለጫቸው አመላክተዋል።
በክልሉ ከ310 ሚሊየን በላይ የፎራፍሬ፣የቡና የእንስሳት መኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተከላ እንደሚካሔድ ኃላፊው አብራርተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ 2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ መንፈቅ አመት የስር መዋቅር የOቃቤ ህግ የድጋፍ ክትትል ሪፖርት ገመገመ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ የ 2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ መንፈቅ አመት የስር መዋቅር የOቃቤ ህግ የድጋፍ ክትትል ሪፖርት ገመገመ።
####################
(ሀላባ ፣ ሰኔ 30/ 2017) የክልሉ ፍትህ ቢሮ ከቢሮው ማኔጅመንት አካላት ጋር የበጀት ዓመቱን የ0ቃቤ ህግ የድጋፍ ክትትል ሪፖርት ግምገማ አካሄደ። ቢሮው የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት እና ተልዕኮውን መሠረት ያደረገ የ 7 ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ በማዘጋጃት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ጥንካሬ እና ድክመት በመገምገም የ 2017 በጀት ዕቅድ ተዘጋጅቶ ባለፉት 12 ወራት ሲተገበር ቆይቷል።
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው ውሳኔ የተሰጠበትን ድንጋጌ አርሞ አፀደቀ
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው ውሳኔ የተሰጠበትን ድንጋጌ አርሞ አፀደቀ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ሰኔ 30 ፣ 2017 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ ልዩ ስብሰባው፤ በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 49 (2)ሀ መሠረት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም በሚል ከሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል፡፡
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው፤ ከአሁን በፊት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አርሞ አፅድቋል፡፡
ለሰብአዊ መብት ጥሰት በር ይከፍታል የተባለው የአዋጅ ድንጋጌ ተሻሻለ
ለሰብአዊ መብት ጥሰት በር ይከፍታል የተባለው የአዋጅ ድንጋጌ ተሻሻለ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 3ኛ ልዩ ስብሰባው፤ በምክር ቤቱ የአሠራር እና የአባላት ሥነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 49 (2)ሀ መሠረት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም በሚል ከሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አፅድቋል፡፡
ምክር ቤቱ በልዩ ስብሰባው፤ ከአሁን በፊት ውሳኔ የተሰጠበት ድንጋጌ እንዲታረም የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ አርሞ አፅድቋል፡፡
የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ያቀረቡ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 37ኛ መደበኛ ስብሰባው፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፤ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1387/2017 አድርጎ ማፅደቁ አስታውሰዋል፡፡
በ2017 በጀት አመት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።
በ2017 በጀት አመት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገለጸ።
(ሆሳዕና፣ ሰኔ 30/2017) ፣ የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮች ከነገ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ግብራቸውን እንዲከፍሉ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።
በ2017 በጀት አመት 16 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል።
ቢሮው እንዳለው በበጀት አመቱ 20 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ከተለያዩ የገቢ አርእስቶች ለመሰብሰብ ታቅዶ እስከ አሁን ባለው ሂደት 16 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል።
የቢሮው ሃላፊ ተወካይና የደንበኞች አገልግሎት የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደግፌ መለሰ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የክልሉ መንግስት ወጪን በሚሰበሰብ ገቢ ለመተካት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የገቢ አማራጮችን ለማስፋት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
የትጋት ምሳሌ ከመሆን እስከ እርቅ አባትነት ስማቸው የሚነሳው የሰላም አባት ሀጂ ከድር
የትጋት ምሳሌ ከመሆን እስከ እርቅ አባትነት ስማቸው የሚነሳው የሰላም አባት ሀጂ ከድር
ሀጂ ከድር ተካ አርሶ አደርና የሀገር ሽማግሌ ናቸው። በባህላዊ ዳኝነት ሥራቸው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የቆዩት ሀጂ ከድር ተካ ዛሬም አንቱታን ያተረፉባቸውን አያሌ ሥራዎች እየሰሩ ይገኛሉ።
ሀጂ በ80ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ናቸው። ውልደታቸውና ዕድገታቸው በስልጤ ዞን፣ ሳንኩራ ወረዳ፣ ዓለም ገበያ ውስጥ ነው።
ሀጂ ከድር ተካ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የተራራቁትን በማቀራረብ በብዙዎች ዘንድ የተመሰከረላቸው አርሶ አደርና የሀገር ሽማግሌም ናቸው።
ገና በወጣትነት የዕድሜ ክልል እያሉ የቀበሌ አስተዳደርና ሚሊሻ ሆነው የሳንኩራን ህዝብ በቅንነት ማገልገላቸውን ብዙዎች ይመሰክራሉ።
ሀጂ ከድር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችሉ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመቀበልና በመተግበር ረገድ ግንባር ቀደም ከሚባሉ አርሶ አደሮች መካከል ናቸው።
የማዕከላዊ #ኢትዮጵያ ክልል #ርዕሰ መስተዳድር #እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሰኔ ወር ያከናወኗቸው #አበይት ጉዳዮች
የማዕከላዊ #ኢትዮጵያ ክልል #ርዕሰ መስተዳድር #እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሰኔ ወር ያከናወኗቸው #አበይት ጉዳዮች
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በተያዘው በጀት ዓመት በሆሳዕና ከተማ ግንባታቸው እየተካሔደ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ምልከታ አድርገዋል።
በከተማው በመገንባት ላይ የሚገኙ የክልል ተቋማት የቢሮ ግንባታ ሂደት ርዕሰ መስተዳድሩ ምልከታ አድርገዋል።
.........................................//.......................................
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር)ለትምህርት ሚኒስትሩ ለብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በጽ/ቤታቸው አቀባበል ያደረጉት ባሳለፍነው የሰኔ ወር ነበር።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ልዩ ልዩ የስራ ክፍሎችን ተመልክተዋል።
ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ግንባታ
ከሰንበት እስከ ሰንበት የገበያ ማዕከል ግንባታ
የኑሮ ውድነት ጫናን በመቀነስ የአምራቹንና ሸማቹን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተግባር መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ
(ሆሳዕና ፣ሰኔ 27/2017) ቢሮው በዱራሜ ከተማ ለሚገነባው ከሰንበት እስከ ሰንበት ዘመናዊ የግብይት ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የማኖር መርሐ ግብር አካሂዷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ እንደገለፁት
የሰንበት ገበያ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በህገወጥ ነጋዴዎች ሳይበዘበዙ ኑሮ ውድነትን ለማቃለል ሳምንቱን በሙሉ የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው ብለዋል።
የህብረተሰቡን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ብሎም አርሶ አደሩን ከሸማቹ ጋር በቀጥታ በማገናኘት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለመ ተግባር እንደሆነም ገልፀዋል።