Skip to main content

የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ማናበብ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በቡታጅራ ከተማ ተጀምሯል።

የከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፕሮጀክት የ2017 በጀት ዓመት  የሥራ  አፈጻጸም ማጠቃለያ እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ማናበብ መርሃ-ግብር በዛሬው ዕለት በቡታጅራ  ከተማ ተጀምሯል።

(ነሐሴ 8/2017 ) በፌዴራል መንግስትና በዓለም ባንክ ድጋፍ በተመረጡ ከተሞች ለመተግበር በተመደበው  በጀት በክልሉ ልዩ ልዩ   ፕሮጀክቶችን በማከናወንና ተጠቃሚዎችን ከተረጅነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር በ2017 በጀት ዓመት የተጀመረውና የተከናወኑ  የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራዎች ላይ  የክልሉ ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት እየገመገመ ነው።

በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል የመድረኩ ዓላማ በከተማ ምግብ ዋስትናና ስራ ፕሮጀክት የተከናወኑ የ2017 በጀት ዓመት ስራዎች አፈጻጸም መገምገምና የ2018 በጀት ዓመት ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ መናበብና የጋራ ማድረግ ነው ብለዋል።

የኢቢሲ ዲጂታል አሠራር እና የይዘት ስብጥር ለሌሎችም ሚዲያዎች አዲሱን ምዕራፍ የከፈተ ነው - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

የኢቢሲ ዲጂታል አሠራር እና የይዘት ስብጥር ለሌሎችም ሚዲያዎች አዲሱን ምዕራፍ የከፈተ ነው - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

(ሆሳዕና፣ ነሃሴ 7/2017)፣ የኢቢሲ ዲጂታል አሠራር እና የይዘት ስብጥር የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ እና ለሌሎችም ሚዲያዎች አዲሱን ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እና የኢቢሲ ቦርድ ሰብሳቢ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናገሩ።

መረጃ የሰዎችን የዕለት ከዕለት ኑሮ በብዙ መልኩ በሚዳስስበት በዚህ ጊዜ፣ ኢቢሲ መረጃን በተለያዩ አማራጮች የሁሉንም መልክ በሚያሳይ መልኩ ተደራሽ ማድረጉ ለኢትዮጵያ ሚዲያ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑንም አንሥተዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ መረጃ በሰከንዶች ልዩነት ዓለምን በሚያካልልበት በዚህ ጊዜ የተዛቡ ትርከቶችን የሚያስተላልፉ በርካቶች እንዳሉም ሚኒስትሩ አንሥተዋል።

በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ16 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቆመ

በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ16 ነጥብ  9  ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቆመ

(ሆሳዕና፣ነሐሴ 7/2017)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ፋይናንሻል እና ፊዚካል ስራዎች አፈጻጸም ፣የክረምት ስራዎች ገቢ አሰባሰብ ለመገምገም እና በ2018 በጀት ዓመት እቅድ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር የሚያስችል የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሔደ ነው

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደግፌ መለሰ እንደገለጹት ክልሉ የሚያመነጨውን ኢኮኖሚ በተገቢው መንገድ ለመሰብሰብ ዘርፈ ብዙ ስራ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

20 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን የገለጹት አቶ ደግፌ በበጀት ዓመቱ ከ16 ነጥብ  9  ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ስለመሰብሰቡ አስረድተዋል።

እንደ ምክትል ኃላፊው ገለጻ በክልሉ ከሌሎች አመታት በተለየ መልኩ ከፍ ያለ ገቢ ለመሰብሰብ የታቀደበት ዓመት እንደነበር አስታውሰዋል።

የፍትሕ ሚኒስቴር የአስተዳደር ፍትሕ ላይ የሚደረጉ ትብብሮችን አስመለክቶ ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ተወካዮች ጋር ዉይይት አካሄደ

የፍትሕ ሚኒስቴር የአስተዳደር ፍትሕ ላይ የሚደረጉ ትብብሮችን አስመለክቶ ከጂ አይ ዜድ (GIZ) ተወካዮች ጋር ዉይይት አካሄደ
******************
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የህግና ፍትሕ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በላይሁን ይርጋ እና የተቋም ግንባታ የሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኤርሚያስ የማነብርሀን (ዶ/ር) ከጀርመን የልማት ተራድኦ ድርጅት (ጂ.አይ.ዜድ) ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር የአስተዳደር ፍትሕ ላይ የሚደረጉ ትብብሮች እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተዉ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም ኢትዮጵያና ጀርመን የፌዴራል መንግስት አወቃቀርን የሚከተሉ አገራት እንደመሆናቸዉ መጠን የሚከተሏቸዉ ስርዓቶችም በዛዉ ልክ ተመሳሳይነት ያላቸዉ መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ አንጻር የአስተዳደር ስነ-ስርዓት ህግ ማርቀቅ ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት ከጀርመን ልምድ የተወሰደ መሆኑን፣ ይህም በተለይ ክልሎች ይህን ህግ በሚያወጡበት ወቅት ትልቅ እገዛ እንዳደረገ ተነስቷል፡፡ 

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚወግነው ለሀገር ብቻ ነው - ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚወግነው ለሀገር ብቻ ነው - ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ

(ነሃሴ 6/2017)፣ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚወግነው ለሀገር እና ለሕገ-መንግስት ብቻ መሆኑን፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ ገለጹ።

ዋና ኮሚሽነሩ አክለውም ከሁሉም ሰው የተሰበሰቡ ሃሳቦች በጋራ ተነጥረው በወጡት ላይ እንመክራለንም ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል እና በዳያስፖራው ማኅበረሰብ አካባቢ አጀንዳ ለመሰብሰብ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።

ማብራሪያውን የሰጡት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ወደ በትግራይ ክልል ሥራዎቹን ለማከናወን ዝግጅቱን በመጨረስ ላይ ይገኛል።

ከዳያስፖራው ማኅበረሰብ ጋርም የምክክር ሥራዎች መጀመራጀውን አንስተው፤ በውጭ ሀገራት የሚደረገው ምክክርም እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በአፍሪካ ትልቁ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በቢሾፍቱ

በአፍሪካ ትልቁ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በቢሾፍቱ

ከ75 ዓመታት  በላይ አፍሪካን ከዓለም ያገናኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጠቀምበት የቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅሙ በዓመት እስከ 25 ሚሊዮን የደረሰ ቢሆንም፤ እያደገ ያለውን የአቪየሽን ፍላጎት ማሟላት አልተቻለም።

ይህን ፍላጎት ለማሟላትም ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ፤ በ10 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የቢሾፍቱ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያን ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

አዲሱን የአውሮፕላን ማረፊያ መገንባት እያደገ ያለውን የአቪዬሽን ዘርፍ ፍላጎት ለሟሟላት፣ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እና ሀገሪቱ በአቪየሽን ዘርፍ መሪነቷን አጠናክራ እንድትቀጥል ያስችላል ብለዋል የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ።

የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ዶ/ር መቅደስ ዳባ

የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ - ዶ/ር መቅደስ ዳባ

( ነሐሴ 6፣ 2017) የአገልግሎት  ጥራትን ለማሻሻል እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ።

የሚኒስቴሩና የክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች የጋራ ምክክር መድረክ በሀረር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተጠናቀቀው የ2017 የበጀት ዓመት በጤናው ዘርፍ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው÷ የጤና አገልግሎት ጥራትን በማሻሻል ረገድ እየተሰሩ የሚገኙ ተግባራትን ለማጠናከር ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።

እንደ ኤፍ ኤም ሲ ዘገባ በቴክኖሎጂ የተደገፉ ስራዎች እውን በማድረግና በቅንጅት በመስራት የተገኙ ውጤቶችን ለማጎልበትና የታዩ ውስንነቶች ለመቅረፍ መረባረብ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር የሉዓላዊነት ጥቃት አካል ነው - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

ሐሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግር የሉዓላዊነት ጥቃት አካል ነው - ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)

(ነሃሴ 6/2017)፣ ኢትዮጵያ ሐሰተኛ መረጃን እና የጥላቻ ንግግርን የብሔራዊ ጥቅም እና የሉዓላዊነት ጥቃት አካል አድርጋ ነው የምትመለከተው ሲሉ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።

ይህን ጥቃት ለማምከን የሚደረገው የተቀናጀ ትግልም በዚያው ልክ ከፍ ያለ ነው ብለዋል በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሀላፊው ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ኤፍኤም አዲስ 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር እንዲሁም በቀጣናው ትክክለኛ እና ፍትሐዊ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናዋን ለመጎናፀፍ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ አቅደው የሚሰሩ  ጠላቶች አሁንም አሉ ሲሉ ዶ/ር ቢቂላ ተናግረዋል።

ለግብርናው ዘርፍ ግቦች ስኬት በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ቁልፍ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ።

ለግብርናው ዘርፍ ግቦች ስኬት በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች ክትትልና ድጋፍ ቁልፍ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገለጸ።

( ሀምሌ 5/2017)፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ከክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርሟል።

በግብርናው ዘርፍ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀመጡ ግቦችን ስኬታማ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች ተከታታይ ክትትልና ድጋፎች ቁልፍ አስተዋጽኦ አላቸው ሲሉ በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ተናግረዋል ።

አቶ ኡስማን የክልሉ ግብርና ቢሮ ከክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጋር በ2018 በጀት አመት የሴክተር እቅድ የግብ ስምምነት ሲፈራረም እንዳሉት ምክር ቤቶች የዘርፉ ወጤቶችና ግቦች መሳካታቸውን ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና አላቸው። የተቀመጡ ቁልፍ ግቦች ተጨባጭ ውጤት ማምጣታቸውን የምናረጋግጥበት ነው ሲሉም አክለዋል።

የዘንድሮው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት የሚከበር ነው - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

የዘንድሮው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት የሚከበር ነው - አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

ነሐሴ 5፣ 2017  የዘንድሮው ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በልዩ ድምቀት የሚከበር ነው አሉ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር።

20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀንን በተመለከተ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በተገኙበት የዐቢይ ኮሚቴ አባላት የመጀመሪያውን የመሪ ዕቅድ ውይይት እያካሄደ ነው።

አፈ ጉባኤ አገኘሁ በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷ 20ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚከበር መሆኑ የለውጡ መንግስት ጥያቄን የመመለስ ተግባራዊ ትሩፋትን የሚያሳይ ነው።

ቀኑ በልዩ ድምቀት የሚከበር መሆኑን አንስተው÷ ለዓመታት በልሂቃን መካከል ሲስተናገድ የነበረው ከፍተኛ የልዩነት ችግር ለመፍታት እንደ ሀገር ምክክር የሚደረግበት መሆኑን ጠቁመዋል።