በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ ጀንበር 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ ጀንበር 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 21፣ 2017 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በአንድ ጀንበር 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል በክልል ደረጃ ዝግጅት ተደርጓል አለ።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በክልሉ 502 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ።
በዓመቱ ከሚተከሉት ችግኞች መካከል 304 ሚሊየን የፍራፍሬ፣ የቡናና የጥምር ደን ሲሆኑ÷ ቀሪ 198 ሚሊየን ችግኞች ደግሞ ለደን ልማት የሚሆኑ ናቸው ብለዋል።
በዚህም 161 ሺህ 925 ሄክታር መሬት ለመሸፈን ዝግጅት ተደርጎ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ስራ እንደሚከናወን ተገለጸ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ስራ እንደሚከናወን ተገለጸ።
(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 21/ 2017)፣ በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ የወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የክልሉ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ በክልሉ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉበት እና ከ86 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ስራ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚከናወን ተናግሯል።
የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ14 ልዩ ልዩ የትኩረት መስኮች የሚከናወን ሲሆን፣ 5 ሺህ ዩኒት ደም ለመለገስ እና 12 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ይሰራል ብሏል።
በልዩ ትኩረት የኢትዮ ኮደርስና ፋይዳ መታወቂያ ንቅናቄ በማካሄድ 500 ሺህ ወጣቶች ግንዛቤ የሚፈጠር እና 28 ሺህ ያህል ወጣቶች ስልጠናውን ሙሉ ለሙሉ አጠናቀው ሰርተፊኬት እንደሚያገኙ ወጣት አብዱ ገልጿል።
ለሕዳሴው ግድብ ድጋፋችንን እናጠናክራለን - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት
ለሕዳሴው ግድብ ድጋፋችንን እናጠናክራለን - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 21/2017)፦ የአብሮነት መገለጫ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት ገለጹ።
ግድቡ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደሚቻል ልምድ የተቀሰመበትና ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሰረት የሚጥል መሆኑን የምክር ቤት አባላቱ ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የክልሉ ምክር ቤት አባላት መካከል በምክር ቤቱ የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ግዛቸው ዋሌሬ የግድቡ ግንባታ ሀገራዊ ልማትን ጀምሮ ማጠናቀቅ እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ ነው ብለዋል።
በተለይ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንዳይሳካ ሲደረጉ የነበሩ ጫናዎችን በመቋቋም በቁርጠኝነትና በአይበገሬነት መሰራቱ ለትውልዱም በፈተና ውስጥ ለሀገር እድገት ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።
ትምህር ቤቶች የአገልግሎት መስጫ ተቋም ብቻ ሳይሆኑ ትውልድ የሚቀረጽባቸውና የሚገነባባቸው ናቸው - አቶ አንተነህ ፍቃዱ
ትምህር ቤቶች የአገልግሎት መስጫ ተቋም ብቻ ሳይሆኑ ትውልድ የሚቀረጽባቸውና የሚገነባባቸው ናቸው - አቶ አንተነህ ፍቃዱ
(ሆሳዕና፦ሀምል 18/2017) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የግልና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤት ባለቤቶች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ምስረታ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ እንደገለፁት የግልና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ቤት ባለቤቶች ማህበር ምስረታ የጋራ ርዕይ የሚጀመርበት ነው ብለዋል።
የጋራ ርዕዩም ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጋራ አመራር መስጠትና ፍትሃዊ የሆነ ትምህርት አሰጣጥን በክልሉ ማረጋገጥ ስለመሆኑም ገልፀዋል።
ትምህር ቤቶች አገልግሎት መስጫ ተቋም ብቻ ሳይሆኑ ትውልድ የሚቀረጽባቸውና የሚገነባባቸው ቁልፍ ተቋማት ናቸው ብለዋል።
"ከመስፈንጠር_ከፍታ_ወደ_ላቀ_እምርታ" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ክላስተሮች የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነው።
"ከመስፈንጠር_ከፍታ_ወደ_ላቀ_እምርታ" በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ክላስተሮች የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነው።
(ሆሳዕና፤ ሐምሌ፣ 18/2017)፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቡታጅራ ክላስተር የህብረቱ የ2017 በጀት ዓመት የፓርቲ ሥራዎች ማጠቃለያ ግምገማ እና የአመራር ምዘና መድረክ በሆሳዕና፣ቡታጅራ፣ ወልቂጤ፣ሀላባና ሳጃ ክላስተሮች እየተካሄደ ይገኛል።
የየክላስተሮችን የተግባር አፈፃፀም የምዘና መድረክ የክላስተር አስተባባሪዎችና የህብረት ሰብሳቢዎች በጋራ እየመሩ ነው።
ምንጭ ፦የክልሉ መ/ኮ
ምክር ቤቱ የ37 እጩ ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ
ምክር ቤቱ የ37 እጩ ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ
ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረቡለት እጩ ዳኞች ሹመት አጸደቀ
ምክር ቤቱ ለከፍተኛ ፍርድ ቤቶች 11 እንዲሁም ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር ፍርድቤቶች ደግሞ 26 በድምሩ የ37 እጩ ጃኞችን ሹመት አጽድቋል።
ላለፉት ሁለት ቀናት ሲካሔድ የነበረው የነበረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ተጠናቋል።
ምንጭ :- የክልሉ መ/ኮ
ምክር ቤቱ የቀረበለትን ደንብና እና አዋጅ መርምሮ አጸደቀ
ምክር ቤቱ የቀረበለትን ደንብና እና አዋጅ መርምሮ አጸደቀ
ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤው የቀረቡለት ልዩ ልዪ ደንቦች እና አዋጆች መርምሮ አጸደቀ
ምክር ቤቱ በከሰዓት ውሎው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የቀበሌ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ አዋጅ እና ለክልሉ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በመጨረሻ አጀንዳው በእጩነት የቀረቡለትን የፍርድ ቤት የዳኞችን ሹመት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ
የውስጥ ኦዲትን በማጠናከር አሰራርን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
የውስጥ ኦዲትን በማጠናከር አሰራርን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው
ምክር ቤቱ በከሰዓት ውሎው የክልሉን ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የኦዲት ሪፖርት ላይ ተወያይቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የውስጥ ኦዲትን በማጠናከር አሰራርን ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል።
ተከታታይነት ያለው የድጋፍና ክትትል ስራ በማከናወን ተገቢ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት በተስተዋሉ የአሰራር ጥሰቶች ፖለቲካዊ፣አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ተችሏል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።
ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 700 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 700 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር። እንዘጋጅ!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 62ሺ 799 መዛግብት ውሳኔ አግኝተዋል - የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 62ሺ 799 መዛግብት ውሳኔ አግኝተዋል - የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት
ሆሳዕና፣ሐምሌ 17/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ በወንጀል እና በፍትሀብሔር 62ሺ 799 መዛግብት ውሳኔ አግኝተዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ በወንጀል እና በፍትሐብሔር ከቀረቡት ጉዳዮች ውስጥ 1ሺ 976 መዛግብት ወደ ቀጣዩ ዓመት ተላልፈዋል።
የፍርድ ቤቶች ውጤታማነትና ቅልጥፍና ከሚለካባቸው ዘዴዎች ውስጥ አንዱ የመዛግብትን የማጥራት አቅም ከፍ አድርጎ መገኘት ስለመሆኑ ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል።