Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አባላት በሳጃ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አባላት በሳጃ ከተማ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ።

(ሆሳዕና፣ሀምሌ 10/2017) ፣በምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ  ሳጃ ከተማ የሚገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አባላት በከተማዋ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።  

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣የየም ዞንና የሳጃ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል።

ምንጭ፦ የክልሉ መ/ኮ

ባሳለፍነው በጀት አመት የክልሉ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና የጋራ እሴቶቻቸውን እንዲያጎለብቱ በልዩ ትኩረት ተሰርቷል- አቶ አቡቶ አኒቶ

ባሳለፍነው በጀት አመት የክልሉ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና የጋራ እሴቶቻቸውን እንዲያጎለብቱ በልዩ ትኩረት ተሰርቷል- አቶ አቡቶ አኒቶ  

(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 10/2017)፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ባሳለፍነው በጀት አመት የክልሉ ህዝቦች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን በአግባቡ ከመጠቀም ባለፈ የጋራ እሴቶቻቸውንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን  እያጎለበቱ እንዲሄዱ በልዩ ትኩረት መሰራቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ ተናግረዋል ።

አቶ አቡቶ የምክር ቤቱ  3ኛ ዙር 11ኛ የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲካሄድ እንዳሉት ምክር ቤቱ የህዝቦችን ህገ መንግስታዊ መብቶች ከማስጠበቅ ባለፈ በጋራ እሴቶች መጎልበት፣ በሰላማዊ ግንኙነትና መስተጋብር፣ በህዝቦች አንድነት፣ የመብትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በማረጋገጥ  ረገድ ግቦችን አስቀምጦ ሲሰራ ቆይቷል።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት እና አስፋልት መንገድ ስራ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት እና  አስፋልት መንገድ ስራ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው

(ሆሳዕና ፣ሐምሌ 10/2017)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)ከሀዲያ ዞን እና ከሆሳዕና ከተማ አመራሮች ጋር በሆሳዕና ከተማ የኮሪደር ልማት እና  የአስፋልት መንገድ ስራ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው ውይይት እያካሔዱ ነው።

በመድረኩ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል ተገኝተዋል።

በሆሳዕና ከተማ ግንባታው እየተካሔደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ከፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ጋር ተቀናጅቶ ተፈጻሚ መሆን በሚችልበት ጉዳይ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እየገመገሙ ነው።

በክልሉ 165 ኪ/ሜ የኮሪደር ልማት ግንባታ ለማካሔድ እየተሰራ መሆኑ ይታወሳል።

ምንጭ :-. የክልሉ መ/ኮ

በህዝቦች መካከል አብሮነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተመላከተ

በህዝቦች መካከል አብሮነትን በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ማጎልበት እንደሚገባ ተመላከተ

ሆሳዕና ፦ሀምሌ 10/2017የማረቆ ልዩ ወረዳ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ማቋቋሚያ የአይነት ድጋፍ አድርጓል

የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ እንደገለጹት  ከዚህ ቀደም የምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ለማጠናከር በገቡት ቃል መሰረት አስር ሰንጋዎች  ቡታጅራ ከተማ በመገኘት ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ድጋፉ ለወንድም እህት ወገን ለሆኑ ለዞኑ ማህበረሰብ አብሮነታችን ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ዞኑን ለማቋቋምና የተሻለ አገልግሎት ለማህበረሰቡ እንዲሰጥ በሚደረገው ጥረት ልዩ ወረዳው  በቀጣይ መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ  የአብሮነታችንና አንድነታችን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በሀብት አጠቃቀምና አስተዳደር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዘገቡን የክልሉ ምክር ቤት የክልሉ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በሀብት አጠቃቀምና አስተዳደር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዘገቡን የክልሉ ምክር ቤት የክልሉ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ

(ሆሳዕና፦ሀምሌ 9/2017) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ፋይናንስ ቢሮ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ አፈጻጸምን ገምግሟል።

የክልሉ ፕላን መሰረተ ልማትና የመንግስት ሀብት ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ታመነ ገብሬ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስትን ሀብት በማስተዳደር ረገድ አበረታች ውጤት ማስመዘገቡን ተናግረዋል።

በራስ አቅም ከዕዳ ነፃ በመሆን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግና የውስጥ ሀብትን በመሰብሰብ የክልሉን ልማት ለማፋጠን በርካታ ስራዎች መሰራቱን በመግለፅ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነዉ፣

ርዕሰ መስተዳድር  እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም  ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነዉ፣
ሆሳዕና ፣ ሐምሌ 9፣ 2017፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ  ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ( ዶ/ር ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮን የሥራ ዘርፎች ሪፎርም ለማድረግ በቀረቡ ጥናቶች ላይ ከቢሮዉ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ይገኛል።

ጥናቶቹ ከተሞችንና ከተሜነትን በዘመነ መንገድ በመምራት ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር  እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ስለመሆናቸዉ ተገልጿል ።

የጥነት ሠነዶቹ በከተምች ፈርጅ ሽግግሮችን ፣ በከተማ ተቋማዊ አደረጃጃትና አሠራሮች ማሻሻያዎችን እና  ፣በከተሞች ከመሬት ጋር የተያያዙ ህገዎጥነቶችን በመከላከል  ዙሪያ ያተኮሩ ሲሆን የጥናት ሠነዶቹ ቀርበዉ ዉይይት እየተካሄደ  ይገኛል።

ምንጭ ፦ የክልሉ መ/ኮ

በዱራሜ ከተማ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ የቦታ ርክክብ ተደረገ።

በዱራሜ ከተማ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ የቦታ ርክክብ ተደረገ።

በተለያዩ ምክንያቶች ኮንትራቱ ተቋርጦ የነበረው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል  በአዲስ መልክ  ጨረታ በማውጣት ለአሸናፊው  ተቋራጭ የሳይት ርክብክብ መደረጉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል ። ግንባታው በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ መሆኑም ተመልክቷል።

የቢሮው ምክትልና  የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሠርካለም ሣሙኤል ተቋርጦ የነበረው የአካል ጉዳተኞች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በየደረጃው ከሚመመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በተደረገው ርብርብ ፕሮጀክቱ በድጋሚ እንዲቀጥል ማድረግ ተችሏል ነው ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

(ሆሳዕና፣ ሀምሌ 9/2017)፣ መከላከያ ሠራዊት አረንጓዴ ዐሻራን ባህል የማድረግ ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ ዐሻራ እና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ዛሬ ተካሂዷል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዚሁ ወቅት፥ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በመከላከያ በኩል 18 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልፀዋል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከዚህ ቀደም በመከላከያ ሠራዊት ተተክለው፣ ለምግብነት የደረሱ የብርቱካን፣ ሎሚ፣ ሮማን፣ ፓፓዬና ሌሎችም ፍራፍሬዎች ለአባላቱ እየቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ  አቶ ጌትነት ታደሰ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደረጉ

(ሆሳዕና፣ሐምሌ 9/2017)የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ  አቶ ጌትነት ታደሰ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የስራ ኋላፊዎች በሆሳዕና ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የክልል ተቋማትን ተመልክተዋል።

በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ የሚደረግበት እና በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ  እየተገነቡ የሚገኙ የክልል ተቋማት  የቢሮ ህንጻ ግንባታ በተያዘው በጀት አመት እየተፋጠነ ይገኛል።

በሰባት የክልል ማዕከል ከተሞች ለሚገነቡ ቢሮዎች መጋቢት 1/2017 የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል።

በተስፋዬ መኮንን

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እያከናወነ ያለው ስራዎች አበረታች መሆኑን የክልሉ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለጸ

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ስርዓት በመዘርጋት እያከናወነ ያለው ስራዎች አበረታች መሆኑን የክልሉ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  ገለጸ
=====

ሀምሌ 9/2017) የምክር ቤቱ የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።

በተመሳሳይ የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እና ሴቶችና ህፃናት ቢሮ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም በቋሚ ኮሚቴዎች ተገምግሟል።

የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ወ/ሰንበት እንደገለፁት ፍርድ ቤቱ የዳኝነት ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ ተግባራትን ለመፈጸም የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል።

የፍርድ ቤቶችን ውጤታማነትና ቅልጥፍና በተመለከተ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እና መዘገብ የመጠራት ስራ በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።